የተጣራ አየር ተቆጣጣሪው አይኪው ኤይር (IQAir) ለሰባተኛ ጊዜ ያደረገውን ጥናት ውጤት በድረ ገጹ አትሟል፡፡ መቀመጫውን በስዊዘርላንድ ባደረገው ድርጅት የጥናት ውጤት መሠረት፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ አብዛኞቹ የዓለም ሀገራት ዜጎች የሚተነፍሱት አየር የተጣራ አይደለም፡፡ መዲናዋ አዲስ አበባ እ.አ.አ በ2024 የከፋ የተበከለ አየር ካለባቸው 8 ሺሕ 954 ከተሞች ዝርዝር ውስጥ 931 ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡
በ138 ሀገራት ውስጥ በሚገኙ 40 ሺሕ የአየር ጥራት መቆጠጠሪያ ጣቢያዎች የሰበሰቡትን መረጃ መነሻ በማድረግ በተሠራው ጥናት፤ ሰባት ሀገራት ብቻ በዓለም ጤና ድርጅት የተቀመጠውን የተጣራ አየር መለኪያ መሥፈርት አሟልተው ተገኝተዋል፡፡ በዚህ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱት አውስትራሊያ፣ ኒውዚላንድ፣ ባሐማስ፣ ባርቤዶስ፣ ግሪናዳ፣ ኢስቶንያ እና አይስላንድ ናቸው፡፡
በአንጻሩ ቻድ፣ ባንግላዴሽ፣ ፓኪስታን፣ ሕንድ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከፍተኛ የተበከለ አየር ያስመዘገቡ ሀገራት ሆነዋል፡፡ ከእነዚህ ሀገራት መካከል ቻድ የተቀመጠውን ዝቅተኛ መለኪያ በ18 እጅ ያነሰ ውጤት አስመዝግባ ከፍተኛውን የተበከለ አየር የያዘች ሀገር ተብላለች፡፡
በመለኪያው የተበከለ አየር አላቸው ከተባለው ሀገራት መካከል ሕንድ 10 ከተሞቿ እጅግ በጣም አስከፊ አየር ካለባቸው በሚል ምድብ ተቀምጠዋል፡፡ የጥናት ውጤት በአሕጉር ደረጃ አስከፊ ውጠየት ስመዝግበዋል ያላቸው አፍሪካ እና እስያን ነው፡፡ በርግጥ በአፍሪካ አንዳንድ ሀገራት የአየር ጥራት መቆጣጠሪያዎች ተደራሽነት አንስተኛ መሆኑ ከዚህም የከፋ ውጤት ሊመዘገብ ይችላል የሚል ጥርጣሬ መኖሩን አይኪው ኤይር ገልጿል፡፡
የሕክምና ባለሞያዎች የተበከለ አየር በሰዎች ጤና ላይ ጉዳት የሚያስክል መሆኑን ይናገራሉ፡፡ የአይኪው ኤይር ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ፍራንክ ሐሜስ እንደተናገረት፤ የአየር ጥራት መጓደል በአንድ ሰው ጤና ላይ የሚፈጥረው እክል በግልጽ ምልክቶችን ለማሳየት ሁለት እና ሦስት ዐስርት ዓመታት ሊፈጅበት ይችላል፡፡ አዝጋሚ የጤና እክል የሚያስከትለው የአየር መበከል፤ ከደም ግፊት በመቀጠል ለሞት መንስዔ ተደርጎ የሚቀመጥ ነው፡፡
መንግሥታት የሚመሩት ሀገር ዜጎች የተሻለ አየር ምገት እንዲኖራቸው ታዳሽ ኃይል ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሠሩ ባለሞያዎች ይመክራሉ፡፡ (ሚንበር ቲቪ)












