ሰኞ , محرم 9, 1446
Google search engine
Homeዜናና ወቅታዊዜናየሬሜዲያል ፈተና የጊዜ ሠሌዳ ለውጥ ማድረጉን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

የሬሜዲያል ፈተና የጊዜ ሠሌዳ ለውጥ ማድረጉን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የጊዜ ሠሌዳውን በተመለከተ ቅሬታ ማቅረቡ ተሰምቷል

የትምህርት ሚኒስቴር የሬሚዲያል (የማካካሻ) ትምህርት የማጠቃለያ ፈተና ላይ የጊዜ ሠሌዳ ለውጥ ማድረጉን ዛሬ ጁመዓ ግንቦት 30/2016 አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ የፈተና ቀን ለውጡን ያደረገው ከዒድ አል አድሓ በዓል ጋር በተመሣሣይ ቀን በመዋሉ ነው ብሏል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ቀድሞ ባስቀመጠው ጊዜያዊ የጊዜ ሠሌዳ ላይ ፈተናው የሚሰጠው ከሰኔ 3 እስከ 10/2016 የነበረ ቢሆንም፣ በአዲሱ የጊዜ ሠሌዳ የአንድ ቀን ጭማሪ ተደርጓል፡፡ በዚህም መሠረት ሰኔ 9 ይሰጥ የነበረው ፈተና ወደ ሰኔ 11 ተዘዋውሯል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር የቀን ለውጥ ያደረገው ሰኔ 9/2016 የዒድ አል አድ በዓል ስለሚከበር መሆኑን ገልጧል፡፡

የትምህር ሚኒስቴር ቀድሞ ያወጣውን የጊዜ ሠሌዳ በተመለከተ ከዒድ አድሓ በዓል ጋር በተመሳሳይ ቀን ከመዋሉ ጋር በተገናኘ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቅሬታ ማቅረቡን ሚንበር ቲቪ ከምክር ቤቱ ኃላፊዎች ሰምቷል፡፡

የትምህር ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ከእስልምና በዓላት ጋር በተመሳሳይ ጊዜ በሚያወጣው የፈተና የጊዜ ሠሌዳ ተደጋጋሚ ቅሬታ የሚቀርብበት ነው፡፡

RELATED ARTICLES

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments