Homeዜናና ወቅታዊዜናየ2017 ረቂቅ በጀት አዋጅ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲመራ ተደረገ

የ2017 ረቂቅ በጀት አዋጅ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲመራ ተደረገ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2017 ረቂቅ በጀት አዋጅ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲመራ ያደረገው ዛሬ ጁመዓ ግንቦት 30/2016 ባካሄደው ስብሰባ ነው፡፡

ምክር ቤቱ የ2017 የፌደራል መንግሥት በጀት የተዘጋጀው የአሥር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል የሆነውን የ2016-2018 የልማትና ኢንቨስትመንት እቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦችንና የ2017-2021 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚና የፊስካል ማዕቀፍን ማስፈጸም እንዲቻል በሚያደርግ መልኩ ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም የ2016 የፌደራል መንግሥትን የፕሮግራም በጀት አፈጻጸም መነሻ በማድረግ፤ የመንግሥት የፋይናንስ አቅም እና ተጠባቂ ገቢዎችን ታሳቢ በማድረግ እንዲሁም አስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች የተሰጣቸውን ተልዕኮና ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስፈልጋቸውን ወጪ በመገምገም እንዲዘጋጅ መደረጉንም ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡

በዚሁ መሠረት ለፌዴራል መንግሥት መደበኛ ወጪዎች፣ ለካፒታል ወጪዎች፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ እና ተጠባባቂ ወጪን ጨምሮ ወደ አንድ ትሪሊዮን የሚጠጋ በጀት ለምክር ቤቱ መቅረቡ ተገልጧል፡፡

ምክር ቤቱም በቀረበው የፌዴራል መንግሥት የ2017 ረቂቅ በጀት አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል ነው የተባለው፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular