እሑድ , ذو الحجة 17, 1445
Google search engine
Homeዜናና ወቅታዊዜናየመጀመሪያዎቹ ኢትዮጵያውያን ሑጃጆች ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ በረራ የሚያደርጉበት ቀን ታወቀ

የመጀመሪያዎቹ ኢትዮጵያውያን ሑጃጆች ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ በረራ የሚያደርጉበት ቀን ታወቀ

መጅሊስ ለተጓዦች ስለ ሐጅ አፈፃፀም የሚሰጠው ሥልጠና በዛሬው እለት ይጀምራል

ለ1445 ዓ.ሂ የሐጅ ሥነ ሥርዐት ከተመዘገቡ ኢትዮጵያውያን ውስጥ የመጀመሪያዎቹ ተጓዦች በረራ የሚያደርጉበት ቀን ታወቀ። “ሚንበር ቲቪ” ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) የሐጅ እና ዑምራ ዘርፍ እንደሰማው የመጀመሪዎቹ ተጓዦች በረራ የሚከናወነው ግንቦት 13፣ 2016 ነው።

ምክር ቤቱ ለዘንድሮው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዐት ለመላክ በእቅድ የያዘው የምዕመናን ቁጥር መጠን 12 ሺሕ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል። “ሚንበር ቲቪ” ከመጅሊስ ኃላፊዎች ማረጋገጥ እንደቻለው በተያዘው ዓመት ለሐጅ ክንውን ወደ ሳዑዲ የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን ምዕመናን ቁጥር ከአምናው በ1 ሺሕ 62 ብልጫ ያለው ነው።

መጅሊስ ለጉዞው የመዘገባቸውን ምዕመናን ከዛሬ ማክሰኞ ሚያዝያ 22/2016 አንስቶ ሥልጠና መስጠት እንደሚጀምር ታውቋል። ይህ ሥልጠና ለስድስት ቀናት የሚቆይ ነው።

የዘንድሮው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዐት ሰኔ 7/2016 ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል። በመላው ዓለም የሚገኙ ወደ 2 ሚሊዮን ገደማ የሚቆጠሩ ምዕመናን ሥነ ሥርዐቱን ለመፈፀም ከግንቦት 1/2016 ጀምሮ ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ መግባት እንደሚጀምሩ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ያመለክታል።

RELATED ARTICLES

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments