Homeዜናና ወቅታዊሰሞነኛ ጉዳዮችአዲስ አበባ የምታስተናግደው “ግራንድ ኢትዮ ዒድ ኤክስፖ”

አዲስ አበባ የምታስተናግደው “ግራንድ ኢትዮ ዒድ ኤክስፖ”

አዲስ አበባ ከተማ ከዐሥር ቀናት በኋላ የዒድ ኤክስፖ እና ባዛር እንደምታስተናግድ ዛሬ ጁመዓ የካቲት 28/2017 በተሰጠ መግለጫ ይፋ ተደርጓል፡፡ አዘጋጆቹ 3 ኢ ኤቨንትስ እና ቢላሉል ሐበሺ የልማት እና መረዳጃ እድር እንዳሳወቁት፤ ኤክስፖው የሚዘጋጀው በዒድ ዋዜማ በሚሊንየም አዳራሽ ነው፡፡ ከመጋቢት 9 እስከ መጋቢት 21/2017 ድረስ ይቆያል የተባለው የዒድ ኤክስፖ፤ ለሁለተኛ ጊዜ የሚከናወን ሲሆን መሪ ቃሉ “የዒድ ዋዜማዎች በሚሊንየም” መሆኑ ተገልጿል፡፡

ለሁለተኛ ጊዜ በሚካሄደው ኤክስፖ ላይ ከ200 በላይ አምራችና ነጋዴዎች እንዲሁም ከ500 ሺሕ በላይ ጎብኚዎች ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡ በዝግጅቱ ላይ የሕጻናት እና አዋቂዎች አልባሳት፣ ልዩ የማፍጠሪያ ምግብ ዐይነቶች እንዲሁም ጉብኚዎች ግብይት ሲፈጽሙ የበጎ አድራጎት ሥራ ላይ እንደሚሳተፉም አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡

ከአዘጋጆቹ መካከል ቢላሉል ሐበሺ የልማት እና መረዳጃ እድር ለመጀመሪያ ጊዜ “የዒድ ዋዜማዎች በሚሊንየም” በሚል መሪ ቃል በተሰናዳው መርሐ ግብር፤ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል የረመዳን መዳረሻ ባዛር ማዘጋጀቱ የሚታወስ ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular