የሶሪያ ደማስቆ ከተማ ነዋሪዎች ከበሻር አል አሰድ አገዛዝ መውደቅ በኋላ የመጀመሪያውን የጁመዓ ሰላት በዛሬው እለት ሰግደዋል፡፡
በሰባተኛው ክፍለ ዘመን በተገነባው ታሪካዊው ኡመያድ መስጅድ በተከናወነው ሳምንታዊው የጁመዓ ሰላት ለመታደም፤ በርካታ ሶሪያዊያን ከደማስቆ ውጭ ካሉ ከተሞች ተጉዘው እዚያ መድረሳቸውን የአልጀዚራው ረሱል ሴርዳር ከሥፍራው ዘግቧል፡፡ የቴሌቪዥን ጣቢያው ዘጋቢ በሰላት ሥነ ሥርዐቱ ላይ ለመታደም ደማስቆ ደርሰዋል ያላቸው የሀገሪቱ ዜጎች ከተነሱባቸው አካባቢዎች መካከል አሌፖ፣ ዴር አዝዞር፣ የበሻር አል አድ ወታደሮች የመርዛማ ኬሚካል ጥቃት ሰንዝሮባታል የምትባለው ምሥራቃዊ ጎዋ ክፍል ይገኙበታል፡፡

የዛሬው የጁመዓ ሰላት መርሐ ግብር በኢማምነት የተመራው በዚህ ሳምንት በባለአደራ ጠቅላይ ሚኒስትርነት በተመረጡት ሙሐመድ አልበሽር ነው፡፡ በጁመዓ ሰላት ላይ የተሳተፉ ሶሪያዊያን የአላህ ሥም ከፍ በማድረግ ስለ ሀገራቸው እና ነጻነት እየዘመሩ እንደነበርም ተገልጿል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)












