Homeዜናና ወቅታዊሰሞነኛ ጉዳዮችየኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መሪዎች የወደብ ድርድር በቱርክ

የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መሪዎች የወደብ ድርድር በቱርክ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሸይኽ ማሕመድ በተያዘው ሳምንት በቱርክ ተገናኝተው ሊመክሩ መሆኑ ተሰምቷል።

ይህንኑ ሚድል ኢስት ዐይ ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ ሁለት ምንጮች ነግረውኛል ብሎ ዘግቧል። የዜና ወኪሉ ያወጣው ዘገባ በሶማሊያ በኩል በተመሳሳይ ቢስተጋባም ከኢትዮጵያም ሆነ የሶማሊያ ባለሥልጣናት ይፋዊ ማረጋገጫ አለማግኘቱን ገልጿል። ንግግሩን ያመቻቻል የተባለው የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ማረጋገጫ አልሰጠም።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከዚህ ቀደም በቱርክ አደራዳሪነት ያደረጉት ሁለት ዙር ውይይት፤ ባለመሥማማት መጠናቀቁን ተከትሎ ድርድሩ ለሦስተኛ ዙር መስከረም ይቀጥላል ተብሎ የነበረ ቢሆንም በተያዘለት የጊዜ ሠሌዳ ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular