የእንግሊዝ መዲና ለንደን የሐላል ምግብ ባንክ አግኝታለች፡፡ ይህ የሐላል ምግብ ባንክ የገንዘብ አቅም በማጣት የእለት ጉርስ ለቸገራቸው የተከፈተ ነው፡፡ መቀመጫውን በከተማዋ ባደረገ ድርጅት የተከፈተው የሐላል ባንክ በአንድ ወር ለ260 ግለሰቦች ሐላል ምግብ አቀርባለሁ ብሏል፡፡
የሐላል ምግብ ባንኩ ከበርካታ የለንደን የንግድ ድርጅቶች የምግብ ልገሣ እንዲሁም ከደቡብ ምዕራብ ኦንታሪዮ እስላማዊ ማዕከል እና ከለንደን የምግብ ባንክ ድጋፍ በመቀበል ላይ ይገኛል። ባንኩ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ የገበታ መደርደሪያዎቼም ሞልተዋል ብሏል፡፡
የሐላል ምግብ ባንኩ በሚቀጥለው ወር ሠፋ ባለ ቦታ እንደሚከፈት ኃላፊዎ ገልጸዋል፡፡ ድርጅቱ የሚያቀርበው የምግብ ድጋፍ ሐላል ምግቦችን ብቻ ለሚመገቡ የተዘጋጀ ቢሆንም ማንኛውም ምግብ የቸገረው ሰው የሚስተናገድበት ነው ተብሏል፡፡
በእስልምና አስተምህሮ መሠረት ሐላል ምግቦችን ለማዘጋጀት የእንስሳት እርድ ከመፈጸም አንስቶ መሥፈርት እንዲሟላ ይጠበቃል፡፡ ከመሥፈርቶች ውስጥ ስለት ያለው መሣሪያ መጠቀም፣ ለእርድ የሚቀርበው እንስሳ ጤናማ አቋም ላይ መገኘት እንዲሁም በአላህ (ሱ.ወ) ሥም መታረዱ ይጠቀሳል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)












