Homeዜናና ወቅታዊሰሞነኛ ጉዳዮች“ፍልስጤማዊያን የነጻነት ታጋዮች” እና ዕድሜ ጠገቡ የእስራኤል ጋዜጣ

“ፍልስጤማዊያን የነጻነት ታጋዮች” እና ዕድሜ ጠገቡ የእስራኤል ጋዜጣ

“ሀአሬትስ” በእስራኤል የሚገኝ ዕድሜ ጠገብ ጋዜጣ ነው፡፡ በ1918 የተመሠረተው ጋዜጣው ለአንባቢያን የሚደርሰው በእንግሊዝኛ እና በሂብሩ ቋንቋዎች ነው፡፡

በዋነኝነት የእስራኤል መሠረት ያለው ጋዜጣው ራሱን ‘ግራ ዘመም አስተሳሰብ ላይ የቆመ’ በሚል የሚገልጽ ነው፡፡ በኤዲቶሪያል ፖለሲው መነሻቸው ከኢትዮጵያ የሆኑ ሰዎችን ጨምሮ ‘ለጭቁኖች ድምጽ እሆናለሁ’ የሚለው “ሀአሬትስ”፤ ደፈር ብሎ የእስራኤሉን ቤንሚን ኔታንያሁን አስተዳደር ይተቻል ተብሎም የሚነገርለት ነው፡፡

ጋዜጣው በዚሀ ሰሞን ከዚሁ ከቤንሚን ኔታንያሁ አስተዳደር ጋር ተላትሟል፡፡ በእለቱ ፍልስጤማዊያን ላይ የቦንብ ጥቃት ከሚሰነዝረው አስተዳደር ጋር የተላተመው አሳታሚው ባደረገው ንግግር ነው፡፡ የጋዜጣው አሳታሚ አሞስ ሾከን ባለፈው እሑድ በለንደን ባደረገው ንግግር ላይ “ፍልስጤማዊያን የነጻነት ታጋዮች” የሚል ሐረግ ተጠቅሟል፡፡ እንደ ሚድል ዐይ ዘገባ ከሆነ ይህን መጠቀሙ በእስራኤል ባለሥልጣት አልተወደደለትም፡፡ አልተወደደለትም ብቻ ሳይሆን ያልገመተውን አስከትሎበታል፡፡ በዚህም የእስራኤል ባለሥልጣናት ስፖንሰር ከመከልከል ጀምሮ ጋዜጣውን ያይጎዳል ያሉትን ሁሉ ቅጣት ጥለዋል፡፡

ጉዳዩ መነጋገሪያ ከሆነና የእስራኤል ባለሥልጣናትም ቁጣቸውን ከገለጹ በኋላ የጋዜጣው አሳታሚ ‘እኔ የነጻነት ታጋይ የሚል ሐረግ ስጠቀም ምናልባት ሐማስን ለማለት ፈልጌም መስሏችሁ ከሆነ አይደለም፤ እኔ የጠቀስኩት ሌሎችን ነው’ ቢልም ሰሚ አላገኘም፡፡ የእስራኤል የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ሽሎሞ ካርሂ በጋዜጣው ላይ ሊጣሉ ይገባል ያለውን ቅጣት የያዘ ዶሴ ለአስፈጻሚው ልኳል፡፡ በዚህም ወትሮም ለሕጻናት እንኳ ጥቂት የማይራሩት የእስራኤል ባለሥልጣናት “ለልጃቸውም” ቢሆን የሚመለሱ እንደማይሆኑ አሳይተዋል እየተባለ ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular