Homeዜናና ወቅታዊሰሞነኛ ጉዳዮችሙስሊም አሜሪካዊያን መራጮች እና ትራምፕ

ሙስሊም አሜሪካዊያን መራጮች እና ትራምፕ

ሊካሔድ ከዐሥር ቀናት በታች በቀሩት የአሜሪካ ምርጫ የመጨረሻዎች የምርጫ ቅስቀሳ መድረኮች እንደቀጠሉ ነው። የምርጫው ተዋናዮች የዴሞክራቲክ ፓርቲዋ ካማላ ሐሪስ እና የሪፐብሊካን ፓርቲው ዶናልድ ትራምፕ ‘እኔ እበልጥ – እኔ እበልጥ’ እየተባባሉ ነው።

አንዱ ሌላውን ለመጣልና ለማብጠልጠል የሚጠቀሟቸው ቃላትም ጠንከር እያሉ ነው። ሰዎቹ ቃላት የሚመርጡት እርስ በእርስ ለመወራወር ብቻ አይደለም። በምረጡኝ ቅስቀሳው ለድምጽ ሲጪዎች ‘እኔ እበጃችኋለሁ’ ለማለትም አማላይ ቃላት ያዘንማሉ።

የኋለኛውን ማድረጉ በዘንድሮው ምርጫ የማጠቃለያ ቀናት ቀድሞ ሙስሊሞችን በተመለከተ ጥሩ መናገር ለማይሆንላቸው ለትራፕም የቀናቸው ይመስላል። ትራምፕ በ2016 በዚህ ወቅት የሚናገሩት የፕሬዚዳንትነት ሥልጣን ከተቆናጠጡ ሙስሊሞች አሜሪካ እንዳይገቡ ገደብ ስለመጣል ነበር። አሁን ግን እየሆነ ያለው እንደዚያ ጊዜው አይደለም።

ትራምፕ ትናንት ምርጫ ቅስቀሳ ባካሔዱበት ሚቺጋን የሙስሊሞችን ሥም በክፉ ማንሳት በመተው “የተከበሩ” ሲሉ የጠሯቸውን የእስልምና መምሕራን ወደ መድረኩ ሲጋብዙ ተስተውለዋል። ሰውዬው ከመድረኩ አስቀድሞም በርካታ የዐረብ እና ሙስሊም መሪዎችን አግኝተው ማነጋገራቸውን ሲኤንኤን ሰምቻለሁ ብሎ ዘግቦ ነበር። የ78 ዓመቱ አዛውንትም ይህንኑ ለሚቺጋን ታዳሚዎች አረጋግጠዋል። የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን እንደጻፉት ከሆነ፣ ውዝግብ በማሳደድ የሚታወቁት ትራምፕ ሙስሊም የሃይማኖት መምሕራን ፊት የሰጧቸው የጋዛን ጉዳይ እንደ እጅ መንሻ ስላቀረቡ ነው።

ተፎካካሪያቸው ዴሞክራቲክ ፓርቲን የጋዛን ጉዳይ መፍታት ተስኖታል በሚል የሚተቹት የቀድሞው ፕሬዝዳንት፣ እኔን ከመረጣችሁ በጋዛ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በመካከለኛውን ምሥራቅ ሰላም አሰፍናለሁ በሚል ደጋግመው ሲናገሩ ተደምጠዋል። ይህ በተለይ በርካታ ሙስሊም መራጮችን በምትይዘው ሚቺጋን የሚገኙ ሙስሊሞችን ልብ ሊያሸፍት ይችላል በሚል መላ ምት እየቀረበ ነው።

ሰሞንኛ መረጃዎች ይህን ቢያመለክቱም ቀድሞ እንደወጡት ከሆነ ሙስሊሞች መራጮች በ2024 ምርጫ ካማላ ሐሪስ የሚወክሉትን ዴሞክራቲክ ፓርቲንም ሆነ ሪፐብሊካኖችን ከመምረጥ ለሦስተኛ አማራጭ ድምጻቸውን ቢሰጡ ይወዳሉ። የአሁኑ የትራምፕ ነገርም የቢቸግር አማራጭ ሆኖ ነው።

ትናንት በሚቺጋን ትራምፕ ጋዛን ጠረጴዛው ላይ ለድርድር ያቀረቡት ትራምፕ፣ በአካባቢው ሙስሊም መሪዎች ‘ድምጽ ስጡት’ በሚል ቅስቀሳ ተደርጎላቸዋል። ከሚቺጋን ሙስሊም ማኅበረሰብ መሪዎች መካከል ታዊቂው ኢማም ቢላል አልዙሃይሪ እንዲያውም ‘ትራምፕን መምረጥ፣ ሰላምን መምረጥ’ ነው ብለዋል።

የሚቺጋን የሙስሊም ማኅበረሰብ መሪዎች እዚህ ትራምፕን መምረጥ ሰላምን መምረጥ ነው ሲሉ፣ በሌላ ጫፍ የዴሞክራቲክ ፓርቲ ሰዎች ‘ከትራምፕ አደገኛነት ራሳችሁን ጠብቁ’ ሲሉ ቀስቅሰዋል። ይህ የተስተጋባው ከካማላ ሐሪስ ጋር በዴሞክራቶች መድረክ የተገኙት በቀድሞዋ የሀገሪቱ ቀዳማይ እመቤት ሚሼል ኦባማ ነው።

የ2024 የአሜሪካ ምርጫ ይካሄዳል ተብሎ ቀጠሮ የተያዘለት ለጥምቅት 26/2017 ነው። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular