Homeዜናና ወቅታዊሰሞነኛ ጉዳዮችለረውዳው ዚያራ የታደሉ ምዕመናን

ለረውዳው ዚያራ የታደሉ ምዕመናን

ሳዑዲ ዐረቢያ ለሐጅ ሥነ ሥርዐት ክንውን የተቀበለቻቸውን ምዕመናን በማስተናገድ ወደ ሀገራቸው እየሸኘች ትገኛለች፡፡ ሀገሪቱ ለዘንድሮ ሐጅ የተቀበለቻቸው ምዕመናን አሐዝ 1.8 ሚሊዮን መሻገሩ መነገሩ ይታወሳል፡፡ በክንውኑ ሒደት በመዲና ከተማ በነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ቤት የተገኙ ምዕመናን የሚታደሉት አንደኛው ጉዳይ ረውዳውን መዘየር ነው፡፡

የሳዑዲ ዐረቢያ መገናኛ ብዙኃን ይዘውት በወጡት መረጃ ለክንውኑ መዲና ከገቡ ምዕመናን መካከል ወደ 1.4 ሚሊዮን የሚጠጉት ረውዳውን ለመዘየር ታድለዋል፡፡

ከጎብኚዎቹ ውስጥ 762 ሺሕ 101 የሚሆኑት ወንድ ምዕመናን ሲሆኑ፣ 641 ሺሕ 539 ሴቶች ናቸው፡፡ እኒዚህ ምዕመናን ረውዳውን የጎበኙት ከዙል ቀዕዳ 1 እስከተያዘው ወር ዙልሒጃ 14 ድረስ ባሉ ቀናት ነው፡፡

በምዕመናን የሚናፈቀው ረውዳ በነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) መስጂድ ሚንበር እና በመኖሪያ ቤታቸው መሃል የሚገኝ ሥፍራ ነው፡፡ 330 ስኩዌር ሜትር የሚሸፍነው ሥፍራ፣ በአንድ ሰዓት ውስጥ 800 ምዕመናንን ማስተናገድ የሚችል ነው፡፡ በነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐ.ወ) “የጀነት ጨፌ” በሚል የተመሠከረለትን ረውዳውን ለመዘየር የታደለ ምዕመን በሥፍራው የሚቆይበት ጊዜ በሰዓት የተገደበ ነው፡፡ በዚህም አንድ ምዕመን በሥፍራው መቆየት የሚፈቀድለት የጊዜ ርዝማኔ ቢበዛ ሠላሳ ደቂቃ ብቻ ነው፡፡

በዘንድሮው የሐጅ ሥነ ሥርዐት ክንውን ወቅት ረውዳውን ለመዘየር የሚፈልጉ ምዕመናን፣ በሥፍራው ለመገኘት ኑሱክ በተሰኘው የሑጃጅ መተግበሪያ ቀጠሮ ማስያዝ ይጠበቅባቸው ነበር፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular