Homeዜናና ወቅታዊዜናመጅሊስ ኢትዮጵያውያን ሑጃጅን በነገው እለት ወደ ሀገር ቤት መመለስ ሊጀምር ነው

መጅሊስ ኢትዮጵያውያን ሑጃጅን በነገው እለት ወደ ሀገር ቤት መመለስ ሊጀምር ነው

ለ1445 ዓ.ሂ የሐጅ ሥነ ሥርዐት ክንውን ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ ያመሩ ምዕመናን ወደ ሀገር ቤት መመለስ ሊጀምሩ ነው፡፡ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) ሥርዐት የመጀመሪያዎቹ ተመላሾች ነገ ረቡዕ ሰኔ 19/2016 በረራ ያከናውናሉ ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያውያኑ ሑጃጅ ወደ ሀገር ቤት የሚያደርጉት በረራ ነገ እንደሚጀመር ያስታወቀው የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ነው፡፡ ምክር ቤቱ የሐጅ ሥነ ሥርዐት በመጠናቀቁ ሑጃጅ ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱበትን ሥራ መጀመሩን ትናንት ሰኞ አስታውቋል፡፡

የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በነገው እለት በረራ የሚያከናውኑት፤ ቀድመው ከኢትዮጵያ ቀድመው ለሐጅ ሥነ ሥርዐት የተነሱ ናቸው ብሏል፡፡ በመጅሊስ ሥርዐት ነገ በረራ ከሚጀምሩት አስቀድመው ትኬት በግል የቆረጡ ምዕመናን ወደ ሀገር ቤት መመለስ የጀመሩት ባለፈው ሳምንት ሐሙስ መሆኑን ሚንበር ቲቪ ሰምቷል፡፡

ኢትዮጵያውያን ሑጃጅ ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ ዝግጅት ሲያደርጉ/EIASC

ለዘንድሮው የሐጅ ሥነ ሥርዐት ክንውን ቀዳሚዎቹ ሑጃጅ ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ የተጓዙት ግንቦት 13/2016 ነበር፡፡ ምክር ቤቱ በተያዘው ዓመት ለክንውኑ የላካቸው ምዕመናን አሐዝ 12 ሺሕ መሆኑም ይታወቃል፡፡

ባለፈው ሳምንት በተጠናቀቀው የሐጅ ሥነ ሥርዐት ከ1.8 ሚሊዮን በላይ ሑጃጅ ከመላው ዓለም ተሳታፊ መሆናቸውን የሳዑዲ ዐረቢያ የሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡ ክንውኑ መጠናቀቁን ተከትሎ ያለፉትን ሳምንታት በቅዱሳኑ መካ እና መዲና ከተሞች ያሳለፉ ምዕመናን ወደ ሀገራቸው መመለስ ከጀመሩ ቀናት ተቆጥረዋል፡፡

የሐጅ ሥነ ሥርዐት ከተጠናቀቀ በኋላ ለክንውኑ ብቻ የተዘጋጀ ቪዛ ያልያዙትን ካልሆነ ማስተናገድ እንደማይችሉ ሲያሳውቁ የቆዩ የሳዑዲ ባለሥልጣናት፣ ከዚህ በኋላ የዑምራ እና ሌሎች ቪዛዎችን የያዙ ግለሰቦችን ማስተናገድ እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

(በዚህ ዘገባ ላይ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ማሻሻያ ተደርጎበታል)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular