እሑድ , ذو الحجة 17, 1445
Google search engine
Homeዜናና ወቅታዊሰሞነኛ ጉዳዮችልዩ “ኸበር” - ከ13 ዓመት በኋላ ዜጎቿን ለሐጅ ሥነ ሥርዐት የላከችው ሀገር

ልዩ “ኸበር” – ከ13 ዓመት በኋላ ዜጎቿን ለሐጅ ሥነ ሥርዐት የላከችው ሀገር

በዚህች ሀገር ከ13 ዓመት በፊት ሐጅ ሲደርስ እንደ ሌሎች ሀገራት ሁሉ ሥነ ሥርዐቱን ለመከወን አቅም አለን ያሉ ምዕመናን መሰናዶ ያደርጉ ነበር።

ከ13 ዓመት በፊት ግን ጉልበት ለመለካካት የተነሱ የሀገሬው ሰዎች ከውጭ ኃይሎች ጋር ተደምረው ባደረሱት ጥፋት ይህ የዘወትር ልማድ ከመከናወን ተገታ። ሀገሪቱ ሶሪያ ነች። ሀገሪቱ የእርስ በእርስ ጦርነት ባመጣባት ጦስ እንዳልነበረች ሆና ዜጎቿ በኢትዮጵያ ጎዳናዎች ላይ መታየታቸውም የተለመደ ሆኖ ነበር።

በሶሪያ ከ13 ዓመታት በኋላ አዲስ ነገር ተሰምቷል። ሀገሪቱ እንደ ቀደመው ዘመን ለሐጅ ሥነ ሥርዐት ዜጎቿን ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ ልካለች። ከደማስቆ የተነሱ ሑጃጆች መሰናዷቸውን አጠናቀው ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ የበረሩት ማክሰኞ ዕለት ነው። ከደማስቆ የተነሳው አውሮፕን 270 ምዕመናንን አሳፍሮ ጅዳ ከተማ ደርሷል።

ሶሪያ ለሐጅ የምትልካቸው ምዕመናን በዚህ ቁጥር የሚቆም አይሆንም። በቀጣይ ሌሎች በረራዎች ምዕመናንን አሳፍረው ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ መብረር እንደሚቀጥሉ የሶሪያ ትራንስፖርት ሚኒስትር ባለሥልጣን የሆኑት ሱለይማን ኸሊል ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።

በርግጥ ከሶሪያ ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ የሚደረገው በረራ ቀጣይነት አይኖረውም። ይህንኑ የሶሪያው ባለሥልጣን ሱለይማን ኸሊል አረጋግጠዋል። ሱለይማን ሲናገሩ “በረራው በሐጅ ወቅት ብቻ የሚገደብ ነው” ብለዋል። ምክንያቱ ደግሞ ፖለቲካ ነው።

በሀገራቱ መካከል ፖለቲካ ጣልቃ ገብቶ ከሐጅ ውጪ በረራ ባይኖርም “ለበይክ” ለማለት በእንግድነት ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ በደረሱ ምዕመናን ፊት የታየው ፈገግታ ግን በፖለቲካ የሚጠይም አልሆነም፤ ደማቅ ነበር። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments