እሑድ , ذو الحجة 17, 1445
Google search engine
Homeዜናና ወቅታዊዜናኅብረተሰቡ ከመጭበርበር የወንጀል ድርጊት እንዲጠነቀቅ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት አሳሰበ

ኅብረተሰቡ ከመጭበርበር የወንጀል ድርጊት እንዲጠነቀቅ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት አሳሰበ

የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ኅብረተሰቡ ከመጭበርበር የወንጀል ድርጊት እንዲጠነቀቅ ማሳሰቢያ ሰጠ። አገልግሎቱ ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 22/2016 ባወጣው መግለጫ አንዳንድ ግለሰቦች እና የወንጀል ድርጊት ፈፃሚዎች የተለያየ ገጽታ ያላቸው ወንጀሎችን በመፈጸም በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ ለማግኘት እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆናቸውን ደርሼበታለሁ ብሏል።

የወንጀል ድርጊቶችን በመፈፀም ገንዘብ ለማግኘት የሚንቀሳቀሱት ግለሰቦች እንደሁኔታው አዋጭነት ሁሉንም የማጭበርበሪያ ስልቶች ይጠቀማሉ ያለው አገልግሎቱ፣ የወንጀል ድርጊታቸውም በሕግ አስከባሪ አካላት በቀላሉ እንዳይደረስበት ራሳቸውን መደበቅ ወይም ከሕግ ዕይታ ለማራቅና ለመሰወር ጥረት እንደሚያደርጉም አመልክቷል።

የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት አጭበርባሪ ናቸው ባላቸው ግለሰቦች በቅርቡ እየተስተዋለ ያለው የወንጀል ድርጊት አፈጻጸም፣ በተለያዩ ሀገራት ተሰማርተው የሚገኙ አንዳንድ ዜጎችን በመቅረብ በሕገ ወጥ መንገድ የውጭ ሀገራት ገንዘብ መሰባሰብ የሕገ ወጥ ሐዋላ የወንጀል ድርጊት ጋር ግንኙነት ያለው መሆኑን ጠቁሟል።

አገልግሎቱ እነዚህ ግለሰቦች ከዚህ ቀደም የኦንላይን እና ልዩ ልዩ ማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም “የትርፍ ጊዜ ሥራ”፣ “አማራጭና አዋጭ ሥራ” እንዲሁም “ኢንቨስትመንት በሚል ማደናገሪያ ስልቶች በመጠቀም ግለሰቦችን በኦንላይን በመቅረብና ግንኙነት በመፍጠር ወደ ማጭበርበሪያ ሰንሰለት ውስጥ በማስገባት ገንዘብ በተለያየ አግባብ ወስደው ሲሰወሩ መቆየታቸውንም አስታውሷል።

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments