Homeዜናና ወቅታዊሰሞነኛ ጉዳዮችለሑጃጆች የተሰናዱት 1 ሺሕ የቁርኣን ጥናት ፕሮግራሞች

ለሑጃጆች የተሰናዱት 1 ሺሕ የቁርኣን ጥናት ፕሮግራሞች

ሳዑዲ ዐረቢያ ለ1445ኛ ዓ.ሂ የሐጅ ሥነ ሥርዐት ክንውን ከመላው ዓለም ምዕመናንን መቀበሏን ቀጥላለች። ሀገሪቱ የምትቀበላቸው የአላህ እንግዶች ከሐጅ በረካ በሚገባ ተቋድሰው ወደመጡበት እንዲመለሱ ያዘጋጀችውን በየጊዜው ይፋ ስታደርግ ቆይታለች።

ከሁለት ሚሊዮን በላይ ለሚገመቱት ምዕመናን አሁን የቀረበው አዲሱ ብፌ ከቁርኣን ጋር የተገናኘ ነው። የሁለቱ ቅዱሳን ሥፍራ መስጅዶች ፕሬዝዳንት እና የመስጅድ አል-ሐረም ኢማም የሆኑት ሸይኽ ዐብዱረሕማን ሱደይስ እንዳስታወቁት፣ በዘንድሮ የሐጅ ክንውን ለሚሳተፉ ምዕመናን በሁለቱም ቅዱሳን ሥፍራዎች (በመካ እና መዲና) 1 ሺሕ የቁርኣን ጥናት ክፍለ ጊዜ ተሰናድቷል። እነዚህ ፕሮግራሞች ለሑጃጆች የተሰናዱት በቆይታቸው ከቅዱስ ቁርኣን ጋር የሚኖራቸውን ቁርኝት ከፍ ለማድረግ በማለም ነው።

በክፍለ ጊዜው ላይ ሑጃጆች የቁርኣን ሒፍዝ ያጠናሉ። ቁርኣን መቅራት እና ትርጉም ከእነማብራሪያ የማድመጥ ዕድልም ይኖራቸዋል። በፕሮግራሞቹ ላይ የሚሳተፉ ሑጃጆች ቁርኣን ለማንበብ የሚቸገሩ ከሆነም በቆይታቸው ይህን ለማሻሻል የሚያግዛቸውን እንዲሁም የቁርኣን ትርጉም ዕውቀታቸው ላይ ክፍተት ካለባቸው ለመድፈን የሚያስችላቸውን ትምህርት ያገኛሉ ተብሏል።

የቁርኣን ሒፍዝ ክፍለ ጊዜው የሚመራው በሳዑዲ ዐረቢያ በቅዱስ ቁርኣን ዕውቀት በተመሰከረላቸው መምሕራን ነው። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular