Homeዜናና ወቅታዊሰሞነኛ ጉዳዮችካዕባ ዛሬ ምሽት በዐዲስ ልብስ ያጌጣል

ካዕባ ዛሬ ምሽት በዐዲስ ልብስ ያጌጣል

ሊጠናቀቅ ጥቂት ሰዓታት ብቻ በቀረው በሒጅሪ ዘመን ቀመር 12ኛው የዙል ሒጃ ወር ዓመታዊው የሐጅ ሥነ ሥርዐት የተስተናገደበት ሆኖ አልፏል፡፡ ለክንውኑ ወደ ቅድስቲቱ መካ ከተማ የተጓዙ ምዕመናን ወደመጡበት ተመልሰዋል፡፡

ሐጅን ያስተናገደው ዙልሒጃ ወር ሲሸኝ፤ ቀጣዩ ወር ዐዲስ ዓመት መጀመሪያውና የተከበሩ ከሚባሉት አንደኛው ሙሐረም ይሆናል፡፡ ከሙሐረም መምጣት ጋር ካዕባ ዛሬ ረቡዕ ምሽት በዐዲስ ልብስ ሊያጌጥ ሽር ጉድ ተጀምሯል፡፡

የታላቁ መስጂድ አስተዳዳሪዎች የሚቀይሩትን የካዕባ ዐዲስ ልብስ (ኪስዋ) ለማዘጋጀት 11 ወራት እንደፈጀባቸው የሳዑዲ ዐረቢያ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡ የልብስ ቅድ፣ የዲዛይን መረጣና ተዛማጅ ሥራዎች ዝግጅቱ የተጀመረው ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ነበር፡፡ የልብስ ዲዛይነሮች፣ የካሊግራፊ ባለሞያዎች እና በልብስ ስፌት የተመሠከረላቸው ባለሞያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ እያንዳንዱን ጨርቅ ቀድድው ሲሰፉ እንከን የለሽ እንዲሆን ጥረት ሲያደርጉ የነበረው ካዕባን ለማስጌጥ ነው፡፡\

የኪስዋው ውጫዊ ንብርብር በጥቁር በተሸለመ ሐር የተሠራ ነው፡፡ በወርቅ እንዲሸፈን ተደርጎ በመቶዎች ኪሎ ግራም የሚመዝን የብር ክር በመጠቀም በሐር ጨርቅ ላይ ከቅዱስ ቁርአን የተወሰዱ 68 ጥቅሶች እንዲያርፉበት ተደርጓል፡፡ ጥቅሶቹ የእስልምና መግለጫዎችን እና የአላህ (ሱ.ወ) ሥሞችን ያካተተ ነው፡፡

ከጥቂት ሣምንታት በፊት የሐጅን መምጣት ተከትሎ ከግርጌ ከፍ የተደረገውን ኪስዋ፤ በየዓመቱ በሙሐረም ዋዜማ ላይ መቀየር የተጀመረው እ.አ.አ በ2022 ነው፡፡ ከዚህ ጊዜ አስቀድሞ ኪስዋ የሚቀየረው በዙልሒጃ ወር 9ኛው ቀን ላይ ነበር፤ በአረፋ ቀን፡፡ ባለፉት ዓመታት በኪስዋ ቅያሪው ወቅት 100 የዕደ ጥበብ ባለሞያዎች ተሳታፊ ሆነው ነበር፡፡

ኪስዋ የዓለማችን ውዱ ልብስ ነው፡፡ የልብሱ ክብደት 850 ኪሎ ግራም ሲመዝን፣ ወጪው ደግሞ 6 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ይገመታል፡፡ የኪስዋ 670 ኪሎ የሚመዝነው ጥቁር ሐር ነው፡፡ በዚህ ሐር ላይ ለሚጻፉ የቁርኣን አንቀፆች 120 ኪሎ 21 ካራት ወርቅ እንዲሁም 100 ኪሎ ግራም ብር ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular