አሜሪካዊው ነርስ ዊልሄልሚ ማሳይ፤ የፍልስጤምን መሬት የረገጠው የበጎ ፍቃድ ነጻ አገልግሎት ለመስጠት ነበር። ወደ ጋዛ ከተማ ከተጓዙ አምስት የጤና ባለሞያዎች መካከል የሆነው ማሳይ፤ በቆይታው በደቡባዊ ጋዛ በሚገኘው ናስር ሆስፒታል እና በሰሜናዊ ክፍል ኢንዶኔዥያ ሆስፒታል ውስጥ ነጻ ድጋፍ ሰጥቷል።
ጋዛ ደርሶ የፍልስጤማዊያንን የዕለት ተዕለት ኑሮ እና የሚያልፉበትን የሕይወት ፈተና ተመልክቶ ለዚህ ሁሉ የማይበገሩ መሆናቸውን መገንዘብ ቻለ። ሰዎቹንም መረመረ። ከዚያም በጽናት መቆማቸው መንፈሣዊ ቅናት እንዳሳደረበት ተናገረ።
በነርስነት የሚያገለግለው ማሳይ፤ ፍልስጤማዊያኑ ጽኑ የሆኑት በእስልምና ላይ በመቆማቸው መሆኑን ማወቅ ቻልሁ ሲል ይናገራል። በእንግድነት በቀረበበት ፖድካስት ጽናታቸውን በምሣሌ ሲደግፈው፦ “እስቲ አስቡት አንዲት እናት አልያም አንድ አባት በእስራኤል ቦንብ የተቀጠፈ ልጃቸውን ተሸክመው እንዴት አልሐምዱሊላህ ማለት ቻሉ?” ሲል ይጠይቃል።
ማሳይ ከዚህ በኋላ ያደረገው ጉዳት እያስተናገዱ ጭምር ‘ተመሥገን’ የሚሉትን ‘የፍልጤማዊያኑን አምላክ’ መፈለግ ነበር፤ በመጨረሻ እስልምናን አገኘ። በፍልስጤማዊያኑ ጽናት የተዋወቀውን እስልምናን ሲገልጸው፤ “የእስራኤል ቦንብ መጋየት የማይችለው ነው” ይላል። (ሚንበር ቲቪ)












