Homeዜናና ወቅታዊሰሞነኛ ጉዳዮችከበዳይ ጎን የቆመው ሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ

ከበዳይ ጎን የቆመው ሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ

የአሜሪካው ሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን ካስመረቀ ሁለት ሳምንት ተቆጥሯል፡፡ በተጠናቀቀው  የትምህር ዘመን የተመረቁ ተማሪዎች ሁልጊዜም በሁሉም የትምህርት ተቋም ውስጥ እንደሚደረገው የትምህርት ማሥረጃቸውን ወስደዋል፡፡ ይህ አሠራር ግን ለሁሉም የሚፈቀድ አይመስልም፡፡ አስመር አስራር ሳፊ እና ሽራዳ ጆሺ ለዚህ ማሳያ ናቸው፡፡

ሁለቱም ያለፉትን አራት ዓመታት በሐርቫርድ ቆይተው ትምህርታቸውን ቢያጠናቅቁም ዲግሪያቸውን ማግኘት አልቻሉም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ፍልስጤምን ደግፈው ሠልፍ በመውጣታቸው ነው፡፡

የዘር ግንዱ ከፓኪስታን የሚመዘዘው አስመር አስራር፣ ሌሎች 12 ተማሪዎች በተመሣሣይ ዲግሪያቸው እንደተያዘባቸው አሁን ካለበት ቦስተን ለአልጀዚራ ዘጋቢ ነግሮታል፡፡ አስመር እንደሚለው እነዚህ ተማሪዎች በተያዘው ዓመት የተመረቁ ብቻ አይደሉም፤ ከመሃላቸው ለአንድ ዓመት ዲግሪያችንን ስጡን በሚል ሲከራከሩ የቆዩ አሉበት፡፡

በመደበኛው አሠራር የሐርቫርድ ምርቃ ሥነ ሥርዐት በተከናወበት እለት ዲግሪያቸውን ማግኘት የነበረባቸው አስመር እና ሽራዳ በአሁኑ ወቅት ለዩኒቨርሲቲው ይግባኝ ጠይቀው ውሳኔ እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡

በተማሪዎቹ አቤቱታ የቀረበበት ሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ እስካሁን ድረስ የእነአስመርን ዲግሪ ለመስጠት አልያም ማብራሪያ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነም፡፡ ይህ ደግሞ ቀጣይ ትምህርታቸው ላይ ጥላውን አጥልቷል፡፡ ከተማሪዎቹ ውስጥ በቴክሳሰ ተወልዳ ያገችው ጆሺ፣ በዩናይትድ ኪንግደም በሚገኘው ኬምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በሶሽዮሎጂ የማስተርስ ዲግሪ ለመቀጠል እቅድ ቢኖራትም የቀድሞ ዩኒቨርሲቲዋ ዲግሪዋን ስለያዘው ስለመሳካቱ ርግጠኛ መሆን ቸግሯታል፡፡

የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ከአንድ ወር በፊት ፍልስጤምን በሚደግፉ ሠልፈኞች ተሞልተው እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ የተማሪዎቹ ድምጽ ወደ አውሮፓ እና አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲች ጭምር ተዛምቷል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular