Homeዜናና ወቅታዊሰሞነኛ ጉዳዮችከ6 ዓመት ሕፃን ዕድሜ የጀመረ የሐጅ ትዝታ

ከ6 ዓመት ሕፃን ዕድሜ የጀመረ የሐጅ ትዝታ

ኤንዶኔዥያዊቷ እናት መርየም ሙሐመድ ሙኒር፣ ከሰሞኑ ሳዑዲ ዐረቢያ ተገኝተዋል፡፡ እናት መርየም ሳዑዲ የተገኙት ለዓመታዊው የሐጅ ሥርዐት ክንውን ነው፡፡ የ66 ዓመት ዕድሜ ያላቸው እናት፣ ከ60 ዓመት በፊት በ6 ዓመታቸው በተመሳሳይ አሁን የተገኙት ሥፍራ ላይ ነበሩ፡፡

ያን ጊዜ ግን ዕድሜያቸው 6 ዓመት ብቻ ነበር፡፡ ክፉ እና ደግ የሚለዩም አልነበሩም፡፡ ወላጆቻቸው ለሐጅ ሲያቀኑ አስከትለዋቸው ነው፡፡

እናት መርየም በ6 ዓመት ዕድሜያቸው ጀምረው በተደጋጋሚ ለሐጅ እና ዑምራ ሳዑዲ ዐረቢያ ተመላልሰዋል፡፡ የሳዑዲ ዜና አገልግሎት እንዳለው ከሆነ ኢንዶኔዥያዊቷ እናት የዘንድሮው ጉዟቸው ለ22ኛ ጊዜ የተከናወነ ነው፡፡

እናት መርየም በእነዚህ ስድስት ዐስርት ዓመታት የቆየ የሐጅ ትዝታቸው ውስጥ፣ የሚያስገርሟቸው ነገሮች ምን እንደሆኑ ተጠይቀው ነበር፡፡ ኢንዶኔዥያዊቷ እናት አንደኛው ጉዳይ ከሀገራቸው ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ ለመጓዝ የመንገዱ ማጠር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

እናት መርየም ከ60 ዓመት በፊት ከወላጆቻቸው ጋር ወደ ሐጅ ሲጓዙ አሁን እንዳደረጉት በአውሮፕላን አልበረሩም፡፡ ባይሆን አነስተኛ መጠን ያላቸው መርከቦች እየተፈራረቁ አድርሰዋቸዋል፡፡ መርከቦቹ ከኢንዶኔዥያ ተነስተው ሳዑዲ ለመድረስ ሕንድን፣ ዐረቢያ እና ቀይ ባህርን ማቋረጥ ነበረባቸው፡፡ እንደ እናት መርየም አገላለጽ ያን ጊዜ የነበረው ከአምስት እስከ ስምንት ሰዓት የሚፈጅ የሐጅ ጉዞ፣ ከሚበላው ገንዘብ እና ጊዜ በተጨማሪ አደገኛ እና አስፈሪ ነበር፡፡ እናት መርየም ከ60 ዓመት በኋላ ከጃካርታ ሳዑዲ ዐረቢያዋ ቅድስት ከተማ መዲና ለመድረስ 9 ሰዓት ከ45 ደቂቃ ብቻ በአየር ላይ በአውሮፕላን በርረዋል፡፡

የእናት መርየም ሀገር ኢንዶኔዥያ፣ በዘንድሮው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዐት እርሳቸውን ጨምሮ 241 ሺሕ ምዕመናንን ወደ ሐጅ ሥነ ሥርዐት ትልካለች፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular