Homeዜናና ወቅታዊዜናየግብጹ አል-አዝሀር “ጥቁር ሽብር” ሲል የጠራውን የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ የፈጸሙትን አዲስ ጥቃት...

የግብጹ አል-አዝሀር “ጥቁር ሽብር” ሲል የጠራውን የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ የፈጸሙትን አዲስ ጥቃት አወገዘ

የግብጹ አል-አዝሀር ዩኒቨርሲቲ፤ “ጥቁር ሽብር” ሲል የጠራውን የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ የፈጸሙትን አዲስ ጥቃት ያወገዘው አዲስ ባወጣው መግለጫ ነው፡፡ ለጥቃቱ በወታደራዊ አደረጃጀት ኃያላን የሚባሉ ሀገራት የሰጡትን  “ሽፋን” ተችቷል፡፡

የተቋሙ መግለጫ የመጣው፤ ማክሰኞ እኩለ ሌሊት (በርካታ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ባወጧቸው መረጃዎች በስሑር ሰዓት) በተፈጸመ የእስራኤል ጥቃት ቢያንስ 450 ንጹሐን ፍልስጤማዊያን ከተገደሉ በኋላ ነው፡፡ በድንኳኖች ውስጥ ተኝተው በነበሩ የጋዛ ንጹሐን ላይ የተፈፀመውን ጥቃት የኮነነው የአልአዝሃር መግለጫ፤ ጥቃቱ የእስራኤልን “አታላይ እና ቃል ኪዳን” አፍራሽ ባሕርይ ለማሳየት ማስረጃ ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑንም ገልጿል፡፡ ፍልስጤማውያንን ከመሬታቸው በማፈናቀል ዒላማ የተደረገ እንደሆነም አክሏል፡፡

የአልአዝሃር መግለጫ ሌላው የጠቀሰው ለእስራኤል ድጋፍ የሚሰጡ ሀገራትን ጉዳይን ነው፡፡ ሀገራት ለወራሪ ድጋፍ መስጠታቸውን “የሥልጣኔ እና የሞራል ውድቀት” ማሳያ ነው ብሎታል፡፡ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ “የጽዮናውያን የግድያ ማሽን” ሲል የጠራቸው የእስራኤልን መሪዎች ላይ በ“ወንጀል እና ጭፍጨፋ” ክስ ለመመሥረት በፍጥነት ርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የእስራኤል ወታደሮች እ.አ.አ ከጥቅምት 2023 አንስቶ በጋዛ በሰነዘሩት ጥቃት፤ ከ48 ሺሕ 500 በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከ112 ሺሕ በላይ መቁሰላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር ዮቭ ጋላንት በጋዛ በሰብአዊነት ላይ በፈጸሙት ወንጀል የእስር ማዘዣ ቢያወጣም እስካሁን ድረስ ተፈጻሚ አልሆነም፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular