በአዲስ አበባ ከተማ የተዘጋጀው የዒድ ኤክስፖ በዛሬው እለት ተከፍቷል፡፡ በሚሊንየም አዳራሽ የተከፈተው ኤክስፖ፤ 3ኢ ኤቨንትስ እና ቢላሉል ሐበሺ የልማት እና መረዳጃ ዕድር በጋራ ያዘጋጁት መሆኑ ተገልጿል፡፡ ኤክስፖው እስከ መጋቢት 21/2017 ድረስ ለ13 ቀናት እንደሚዘልቅ አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡
ኤክስፖውን ሲከፈት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እንዲሁም የባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የዒድ አል ፊጥር በዓልን በማስመልከት እንደተሰናዳ የተገለጸው መድረክ፤ የመገበያያ አማራጭ ከመሆኑ በተጨማሪ ኢስላማዊ ቅርሶች የሚጎበኙበት፣ ኢትዮጵያዊ ማንነት የሚታይበት እና ለተለያዩ በጎ አድራጎት ሥራዎች ዕድል የሚፈጠርበት መሆኑንም አክለዋል፡፡
በኤክስፖው ላይ ከ150 በላይ የንግድ ኩባንያዎችን ለማስተናገድ ቦታ መዘጋጀቱን የገለጹት አዘጋጆቹ፤ እያንዳንዳቸው አልባሳት፣ የሥነ ጥበብ ሥራ፣ የቤት እቃ እና ዘርፈ ብዙ ቢዝነስ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ይሳተፉበታል ብለዋል። ኤክስፖው በሚቆይቸው ቀናት ከጧት 3 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ድረስ ማኅበረሰቡ እንደሚስተናገድም ታውቋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)












