Homeየቲቪ ፕሮግራሞችበነገው እለት ለሚካሔደው ሀገር አቀፍ የቁርኣን ውድድር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ጠቅላይ ምክር...

በነገው እለት ለሚካሔደው ሀገር አቀፍ የቁርኣን ውድድር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ጠቅላይ ምክር ቤቱ ገለጸ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላም ምክር ቤት፤ ነገ እሑድ በአዲስ አበባ አብዮት አደባባይ ለሚያካሔደው የቁርኣን ውድድር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል። የምክር ቤቱ ኃላፊዎች የኢፍጣር መርሐ ግብር በጋራ እንደሚካሄድ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ይህን ያስታወቀው ዛሬ ቅዳሜ መጋቢት 6/2017 በቅጽር ግቢ በተሰጠ መግለጫ ነው። መግለጫውን የሰጡት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ፤ ሀገር አቀፍ የሒፍዝ ውድድሩ ለቁርኣን ያለንን ክብር የምናሳይበት እንዲሁም ቁርኣን የሰው ልጆች የሕይወት መመሪያ መሆኑን በተገኘው አጋጣሚ የምናረጋግጥበት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህ መርሐ ግብር ላይ የጎዳና ኢፍጣር ፕሮግራም እንደሚኖር አያይዘው የተናገሩት ኡስታዝ አቡበከር፣ አብሮነትን ለማሳየት በሚል ዓላማ የሚሰናዳ መሆኑንም አስረድተዋል።

ለሀገር አቀፍ የቁርአን ውድድር በተደረገ ማጣሪያ ከወንድ እና ሴት ተሳታፊዎች ለሁለቱም ጾታ ሦስት ተወዳዳሪዎች እንደተለዩ የገለጹ ሲሆን፣ በውድድሩ አሸናፊ ለሚሆኑ የተሽከርካሪ፣ የሐጅ እና የገንዘብ ሽልማት ይበረክታል ተብሏል።

ሀገር አቀፍ የቁርኣን ሒፍዝ ውድድር እና የጎዳና ላይ ኢፍጣሩ በተሳካ ሁኔታ እንዲከናወን ኢስላማዊ ሥነ ምግባርን በተላበሰ መልኩ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ ምክር ቤቱ አሳስቧል። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular