Homeዜናና ወቅታዊዜናሸሪዓውን መሠረት ያደረገ የኢንሹራንስ አገልግሎት የሚሰጠው አማና ኢንሹራንስ የፈራሚዎች ጉባኤ አካሔደ

ሸሪዓውን መሠረት ያደረገ የኢንሹራንስ አገልግሎት የሚሰጠው አማና ኢንሹራንስ የፈራሚዎች ጉባኤ አካሔደ

ሙሉ ለሙሉ ሸሪዓውን መሠረት ያደረገ የኢንሹራንስ አገልግሎት የሚሰጠው አማና ኢንሹራንስ፤ የፈራሚዎች ጉባኤ ያካሄደው የካቲት 23/2017 ነው፡፡ በአዲስ አበባ አያ ሆቴል በተካሄደው መርሐ ግብር ላይ የአደራጅ ኮሚቴው ሪፖርት ቀርቧል፡፡

አማና ኢንሹራንስ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የምሥረታ ፍቃድ ከወሰደ በኋላ በአክሲዮን በሽያጭ ሒደት ከአነስተኛ 200 አክሲዮን ወይም 200 ሺሕ ብር ጀምሮ ከፍተኛውን ደግሞ 2 ሺሕ አክሲዮን ማለትም 12 ሚሊዮን ብር ሲሸጥ ነበር ተብሏል፡፡

አክሲዮን ማኅበሩ 68 ሚሊዮን 60 ሺሕ የተከፈለ ካፒታል እና 260 ሚሊዮን 60 ሺሕ የተመዘገበ ካፒታል መሰብሰቡንም የአደራጆች ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሑሴን ሰብሪ ሲራጅ ባቀረቡት ሪፖርት አስተረድተዋል።

በኢትዮጵያ ሲቋቋም የመጀመሪያው መሆኑ በተገለጸው ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነጻ አገልግሎት የሚሠጠው የኢንሹራንስ ዐይነት፤ ከባለ አክሲዮኖች ባሻገር ደንበኞችንም ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን አቶ ሑሴን ለሚንበር ቲቪ ተናግረዋል።

የኢንሹራንስ ኩባንያው ካደረገው የፈራሚዎች ጉባኤ በኋላ የጉባዔውን ቃለ ጉባኤ ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ሠነዶችን ለብሔራዊ ባንክ እንዲቀርብ ከተደረገ በኋላ አገልግሎት ለማስጀመር የሚደረጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በሒደት ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡

ሰብሳቢው አገልግሎቱን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ ኅብረተሰቡ አገልግሎቱን እንዲጠቀም እንዲሁም ሌሎች ከወለድ ነጻ አገልግሎቱ የሚሰጡ የኢንሹራስ ተቋማት እንዲመሠረቱ እገዛ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አማና ኢንሹራንስ አ.ማ የፈራሚዎች ጉባኤውን ሲያጠናቅቅ 11 አባላት እና 4 ተጠባባቂዎችን በመምረጥ ቦርዱን በመሠየም ቃለ ጉባዔውን አጽድቋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular