የፍልስጤሙ ሐማስ ከእስራኤል ጋር የሚያደርገው የተኩስ አቁም ድርድር፤ ሁለተኛ ዙር መጀመሩን ያስታወቀው የአደራዳሪዋ ግብጽ ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ነው፡፡
አደራዳሪዎቹ የንጹሐንን ሥቃይ ለማቃለል፣ በቀጣናው መረጋጋትን ለማምጣት እንዲሁም ሰብዓዊ ርዳት በሚሻሻልበት መንገድ ላይ ውይይት እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የሐማስ እና እስራኤል ተኩስ አቁም ሁለተኛ ዙር ድርድር መጀመሩ ይፋ የተደረገው ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ የመጀመሪያው ዙር ማጠናቀቂያ ቀን መሆኑ ከተገለጸ በኋላ ነው፡፡
በጋዛ ተኩስ አቁም ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ሐማስ ምርኮኞችን በመልቀቅ 644 ፍልስጤማዊያን እንደሚለቀቁ የተገለጸ ቢሆንም የእስራኤል ባለሥልጣናት ፍልስጤማዊያኑን ያስረከቡት ትናንት ሐሙስ ነው፡፡ ነጻ ከወጡት መካከል 600 ፍልስጤማዊያን ቀድመው ሲለቀቁ፤ ሕጻናት እና እናቶችን ለመልቀቅ የእስራኤል ባለሥልጣናት ዘግይተዋል፡፡ በመጨረሻ ሕጻናቱ እና እናቶች ተለቀው ከቤተሰብ ጋር መቀላቀል ችለዋል፡፡
የሐማስ እና እስራኤል ተኩስ አቁም አደራዳሪዎች ኳታር፣ ግብጽ እና አሜሪካ መሆናቸው የሚታወቅ ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)












