Homeዜናና ወቅታዊዜናትራምፕ በማኅበራዊ ገጽ ያጋሩት በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተፈበረከ የጋዛ ቪድዮ ተቃውሞ ገጠመው

ትራምፕ በማኅበራዊ ገጽ ያጋሩት በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተፈበረከ የጋዛ ቪድዮ ተቃውሞ ገጠመው

የአሜሪካው የሙስሊሞች መብት ተሟጋች፤ ‘ዘ ካውንስል ኦን አሜሪካን ኢስላሚክ ሪሌሽንስ’ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተፈበረከ የጋዛ ከተማ ቪድዮ ማሠራጨታቸውን ተቃውሞ መግለጫ አውጥቷል፡፡

በተፈበረከው ቪድዮ ትራምፕ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር በተራቆተ አላበበስ በጋዛ ሐይቅ ዳርቻ ‘ሲዝናኑ’ ይታያል፡፡ በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ አወዛጋቢ ሚና አለው የሚባለው ቱጃሩ የፕሬዝዳንቱ ወዳጅ ኤሎን መስክም በቪድዮው ገንዘብ ሲበትን ይታያል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከእስልምና አስተምሕሮ ያፈነገጡ ምስሎች የቪድዮው ትዕይንት አካል ተደርገዋል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው ከሆነ፤ ቀድሞ ይፋዊ ባልሆኑ የዋይት ሐውስ ኢ መደበኛ መገናኛ ብዙኃን የተሠራቸው ቪድዮ፤ ከቆይታ በኋላ ትሩዝ ሶሻል በተሠኘው የትራምፕ ማኅበራዊ ትስስር መድረክ እንዲጋራ ተደርጓል፡፡

ዘ ካውንስል ኦን አሜሪካን ኢስላሚክ ሪሌሽንስ ይህን ተቃውሞ ባወጣው መግለጫ፤ ትራምፕ ሰላም የማምጣት ፍላጎት ካላቸው “በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተፈበረከ ቅዠት ማጋራት መተው አለባቸው” ብሏል፡፡ የመብት ተሟጋቹ ትራምፕ ይህን ድርጊት በማቆም ጋዛን ጨምሮ ነፃና ገለልተኛ የሆነ ፍልስጤማዊ መንግሥት ለመመሥረት ጥረት ማድረግ እንደሚኖርባቸው አሳስቧል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት ዳግም ሥልጣን ከጨበጡ በኋላ ካሳለፏቸው አወዛጋቢ የፖሊሲ ውሳኔዎች በተጨማሪ፤ በፍልስጤም መሬት በጋዛ ከተማን የሚገኙ ነዋሪዎችን በሌላ ቦታ የማሥፈር እቅድ እንዳላቸው መናገራቸው ተቃውሞ አስነስቷል፡፡

የጋዛ ነዋሪዎችን ለማሥፈር የታጩት ግብጽ እና ጆርዳን መሆናቸው ይታወቃል፡፡ እቅዱን የተቃወሙ ሙስሊም እና ዐረብ ሀገራት በቀጣዩ ሳምንት በጋዛ ጉዳይ የሚመክር ውይይት ለማድረግ ዐረብ ሊግ አስቸኳይ ጉባዔ ጠርቷል፡፡ የዐረብ ሊግ ጉባዔ ከመከናወኑ አስቀድሞ የሁለቱን ሀገራት መሪዎች ያሳተፈ ውይይት በሳዑዲ ዐረቢያ ተካሔዷል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular