Homeዜናና ወቅታዊዜናየጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ ፍልስጤምን አምባሳደር ማነጋገራቸውን ጽሕፈት ቤታቸው ገለጸ

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ ፍልስጤምን አምባሳደር ማነጋገራቸውን ጽሕፈት ቤታቸው ገለጸ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም፤ በኢትዮጵያ የፍልስጤም አምባሳደር ፋሬስ አልቁብን ተቀብለው ማነጋገራቸውን ጽሕፈት ቤታቸው በዛሬው እለት አስታውቋል፡፡ እንደ ምክር ቤቱ መረጃ ከሆነ፤ በኢትዮጵያ የፍልስጤም አምባሳደር ፋሬስ አልቁብ እና የአምባሳደሩ ዋና ጸሐፊ ዲያዲን አል ናሙራህ በጠቅላይ ምክር ቤቱ ተገኝተው በፍልስጤም ሰላም ዙሪያ ከፕሬዝዳንቱ ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ውይይት ላይ ፍልስጤማዊያን ጸንቶ የመታገል ተምሣሌት፣ በአላህ የመመካት እንዲሁም ትዕግሥትን ለዓለም በተግባር ያሳዩ መሆናቸውንም ፕሬዝዳንቱ አንስተዋል፡፡ በተጨማሪም ባለፈው ሳምንት የተደረሰው የጋዛ ተኩስ ስምምነት በውይይቱ ላይ ሌላኛው ጉዳይ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፣ በስምምነቱ ጦርነት እንዲቆምና ሰላም እንዲሰፍን ያለመታከት አደራድረዋል ላሏቸው አካላት ምሥጋና አቅርበዋል ሲል ምክር ቤቱ ባወጣው መረጃ ላይ አስፍሯል፡፡

የፍልስጤም በኢትዮጵያ አምባሳደር ፋሬስ አልቁብን በውይይቱ ወቅት ከነፃነት ትግል ጋር የተያያዘ ነው ባሉት የፍልስጤም ሕዝብ ታሪክ፤ ከሰሞኑ የተደረሰው የተኩስ አቁም ተግባራዊ መደረጉ እንዳስደሰታቸውና የተኩስ አቁሙ ሰላም ዘላቂ እንዲሆን በመላው ዓለም የሚገኙ ሙስሊሞች ዱዓ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ባለፈው ሳምንት አጋማሽ የተደረሰውን የጋዛ ተኩስ አቁም ተከትሎ ባለፈው እሑድ ከእኩለ ቀን በኋላ፤ ስምምነቱ ተግባራዊ ተደርጎ 90 ፍልስጤማዊያን ከእስራኤል ወሕኒ ቤቶች ነጻ መውጣታቸው ይታወቃል፡፡

ፍልስጤማዊያኑ የተለቀቁት በሦስት ዙር ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው ተኩስ አቁም በቀዳሚው ስምምነት መሠረት ነው፡፡ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ሲደረግ ቢያንስ 1 ሺሕ ፍልስጤማዊያን ነጻ ይወጣሉ ይጠበቃል፡፡ በስምምነቱ ሐማስ 33 ምርኮኞችን ይለቃል የተባለ ሲሆን፣ በእያንዳንዱ ምርኮኛ 30 ፍልስጤማዊያን የሚለቀቁ ይሆናል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular