Homeዜናና ወቅታዊዜናየሙስሊም ተማሪዎችን የሒጃብ ክልከላ የተቃውሞ ሠልፍ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እንዲቀላቀሉት ምክር ቤቱ...

የሙስሊም ተማሪዎችን የሒጃብ ክልከላ የተቃውሞ ሠልፍ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እንዲቀላቀሉት ምክር ቤቱ ጥሪ አቀረበ

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፤ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአክሱም ሒጃብ ለብሰው ትምህርት ቤት እንዳይገቡ የተደረጉ ተማሪዎችን አስመልክቶ በተዘጋጀው የተቃውሞ ሠልፍ ላይ ተገኝተው ድምጻቸውን እንዲያሰሙ ጥሪ አቅርቧል። ምክር ቤቱ መገናኛ ብዙኃን እና የፖለቲካ ፓርቲዎችም እንዲሳተፉ ጋብዟል።

የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጥሪውን ያቀረበው ዛሬ ቅዳሜ ጥር 10/2017 ነው። በቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ ጥር 13/2017 የሚካሔደው የተቃውሞ ሠልፍ የሚከናወነው በትግራይ ክልል መቀመጫ መቐለ ከተማ ሮማናት አደባባይ መሆኑንም አስታውቋል።

በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ በትምህርት ቤቶች የተጣለውን የሒጃብ ክልከላ የሚቃወም ሕዝባዊ ሠልፍ በቀጣይ ሳምንት እንደሚካሔድ ያስታወቀው ጥር 8/2017 ነበር። ቀድሞ የተቃውሞ ሠልፉን ለማድረግ ቀጠሮ ተይዞ የነበረው ጁመዓ ጥር 9 የነበረ ቢሆንም የጊዜ ሠሌዳው ከሌላ ሃይማኖታዊ በዓል ጋር በመገጣጠሙ የቀን ለውጥ ተደርጎበታል።

ምክር ቤቱ ከዚህ ቀደም የሒጃብ ክልከላውን በተመለከተ ታኅሣሥ 25/2017 በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ጉዳዩ እልባት የማይሰጠው ከሆነ “ወደ ቀጣይ ርምጃ” እንደሚሻገር ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡

በአክሱም ከተማ በተማሪዎች ላይ የሒጃብ ክልከላውን ጥለውታል የተባሉት ትምህርት ቤቶች “አክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት”፣ “ወርኢይ”፣ “ክንደያ”፣ “ኣብርሃ ወ ኣጽብሃ” እና “አሉሚናይ” ናቸው፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular