Homeዜናና ወቅታዊዜናየትግራይ ክልል ት/ቢሮ አለባበስን በተመለከተ ያሳለፈው ውሳኔ ግልጽነት የሚጎድለው ነው ተባለ

የትግራይ ክልል ት/ቢሮ አለባበስን በተመለከተ ያሳለፈው ውሳኔ ግልጽነት የሚጎድለው ነው ተባለ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሙስሊም ተማሪዎችን በተመለከተ ያሳለፈው ውሳኔ ግልጽነት የጎደለው መሆኑን ተማሪዎች እና ወላጆች ገልጸዋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ዛሬ ሐሙስ ጥር 8/2017 ለአክሱም ከተማ ትምህርት ቢሮ የተማሪዎችን አለባበስ በተመለከተ በጻፈው ደብዳቤ ከትምህርት ገበታ ውጪ የተደረጉ ተማሪዎች ቀድሞ የነበረውን አለባበስ ተጠቅመው ትምህርት እንዲቀጥሉ ውሳኔ አሳልፏል። ነገር ግን በደብዳቤው ላይ ሒጃብ መፈቀድ አልያም አለመፈቀዱን በግልጽ አልሠፈረም።

በክልከላው ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጪ ለመሆን የተገደዱ ተማሪ እና ወላጆች ለሚንበር ቲቪ እንደተናገሩት፤ የክልሉ ትምህርት ቢሮ የጻፈው ደብዳቤ ከ15 ቀናት በፊት እንደጻፈው ደብዳቤ ለትርጉም ክፍት ተደርጎ የተዘጋጀ ነው። እንደ ተማሪ እና ወላጆች ከሆነ፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ታኅሣሥ 22/2017 ለአክሱም ትምህርት ቢሮ በጻፈው ደብዳቤ አለባበስን በተመለከተ አዲስ መመሪያም ሆነ እግድ እንደማይቀበል ገልጾ በነባሩ አሠራር እንዲቀጥሉ ማሳሰቢያ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ወደ ትምህርት ቤት ቢያመሩም እንዲመለሱ ተደርገዋል።

በወቅቱ ዳግም ክልከላ የጣሉ ትምህርት ቤቶች አስተዳዳሪዎች ቢሮው በጻፈው ደብዳቤ ሒጃብ መፈቀዱን በግልጽ አላሠፈረም የሚል ምክንያት ጠቅሰው ነበር። የትምህርት ቤት አስተዳዳሪዎች ለሁለተኛ ጊዜ ለተጻፈው ደብዳቤ አዎንታዊ ምላሽ የሚሰጡ ከሆነ በነገው እለት ወደ ትምህርት ቤት እንደምታመራ ለሚንበር ቲቪ የተናገረች ሥሟ ለደኅንነቷ ሲባል እንዳይጠቀስ የፈለገች ተማሪ ተናግራለች።

በአክሱም ከተማ ሴት ተማሪዎች በትምሕርት ቤቶች በተጣለው ሒጃብ ክልከላ ምክንያት ከትምሕርት ገበታ ውጪ የሆኑት ከታኅሣሥ 8/2017 አንስቶ ነው፡፡

የተጣለውን የሒጃብ ክልከላ ሲቃወም የቆየው የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፤ በቀጣይ ሳምንት ሠልፍ እንደሚካሔድ አስታውቋል፡፡ ምክር ቤቱ ሠልፉ የሚካሔደው ማክሰኞ ጥር 13/2017 እንደሚሆን ይፋ አድርጓል፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular