Homeዜናና ወቅታዊዜናየአውሮፓ ኅብረት ሀገራት በሶሪያ ላይ የጣሉትን ማዕቀብ ለማንሳት ከሁለት ሳምንት በኋላ ቀጠሮ...

የአውሮፓ ኅብረት ሀገራት በሶሪያ ላይ የጣሉትን ማዕቀብ ለማንሳት ከሁለት ሳምንት በኋላ ቀጠሮ ያዙ

የአውሮፓ ኅብረት ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሶሪያ ላይ የጣሉትን ማዕቀብ ለማንሳት ከሁለት ሳምንት በኋላ ጥር 19/2017 ለመገናኘት ቀጠሮ መያዛቸውን አሳወቁ፡፡ የኅብረቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ይህን ውሳኔ ያሳለፉት፤ የሶሪያው የቀድሞ ፕሬዝዳንት በሻር አል አሰድ ወደ ሞስኮ ከኮበለሉ በኋላ በሳዑዲ ዐረቢያ ሪያድ ከተማ በተደረገው ጉባዔ በላይ ነው፡፡

በጉባዔ ላይ የአውሮፓ ኅብረት ተወካይን ጨምሮ አዲሱ የሶሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሰድ ሐሰን እና የመካከለኛው ምሥራቅ ባለሥልጣናት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ለጋዜጠኞች የተናገሩት የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ ካጃ ካላስ፤ የኅብረቱ አባል ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በቤልጅየም ብራሰልስ ከተማ የሚገናኙበት ቀን ተቆርጧል፡፡

የአውሮፓ ኅብረት በሶሪያ ሁሉንም ያካተተ መንግሥት እንዲመሠረት ፍላጎት እንዳለው የገለጹት ኃላፊዋ፤ በሀገሪቱ ላይ የተጣለው ማዕቀብ በፍጥነት መነሳት እንደሚኖርበትም አሳስበዋል፡፡ ለዚህ መነሻ ሆኗል ያሉት አዲሱ የሶሪያ አስተዳደር የሴቶችንና ሌሎችንም መብቶች የሚያከብር መሆኑ ነው፡፡ ከጉባኤው በኋላ የአውሮፓ ኅብረት አባል የሆኑ ስድስት ሀገራት በሶሪያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ በይፋ መጠየቃቸውን ሬውተርስ የዜና ወኪል ዛሬ ሰኞ ዘግቧል፡፡ የማዕቀቡን መነሳት የሚደግፈውን ሠነድ የፈረሙት ሀገራት ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ኔዘርላንድስ፣ ስፔን፣ ፊንላንድ እና ዴንማርክ ናቸው፡፡

ትናንት እሑድ ጉባዔውን ያስተናገደችው ሳዑዲ ዐረቢያ፤ በተመሣሣይ በሶሪያ ተጥሎ የቆየው ማዕቀብ እንዲነሳ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ጥሪ አቅርባለች፡፡ በሪያድ ጉባዔ ከተሳተፉት መካከል የግብጽ፣ የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች፣ ኳታር፣ ባሕሬን፣ አራቅ፣ ዮርዳኖስ፣ ባህሬን፣ ኢራቅ፣ ሊባኖስ እና ቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ይገኙበታል፡፡ ከአውሮፓ ሀገራት ደግሞ የብሪታንያ እና ጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሲሳተፉ፤ አሜሪካ እና ጣሊያን በምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተካፍለዋል፡፡

ሶሪያን በአሁኑ ሰዓት የሚመራው ሐያት ተሕሪር አል ሻም የተሰኘ ቡድን መሆኑ ይታወቃል፡፡ የቡድኑ መሪ አሕመድ አል ሹራ ሥልጣን ከያዙ በኋላ ከ14 ዓመታት የከፋ የእርስ በእርስ ጦርነት በኋላ ሀገሪቱን መልሶ ለመገንባት በቀድሞው አገዛዝ ዘመን በተለያዩ ሀገራት የተጣሉ ማዕቀቦች እንዲነሱ ሲጠይቁ ቆይተዋል፡፡

የሶሪያ የንግድ ሚኒስትር ማሒር ካሊል አል ሐሰን ለመገናኛ ብዙኃን እንደገለጹት፤ በጦርነት የተጎዳችውን ሀገር በኢንዱስትሪ፣ በኃይል እና ኢንቨስትመንት መልሳ እንድታንሰራራ ለማድረግ ማዕቀቡ ካልተነሳ “ሁኔታዎች አስቸጋሪ” ይሆናሉ፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular