Homeየቲቪ ፕሮግራሞች“ቢላል” እና “ጄይሉ”ን ጨምሮ ሦስት ኢስላማዊ መገናኛ ብዙኃን በመዋሐድ “ነጃሺ ቲቪ” የተሰኘ...

“ቢላል” እና “ጄይሉ”ን ጨምሮ ሦስት ኢስላማዊ መገናኛ ብዙኃን በመዋሐድ “ነጃሺ ቲቪ” የተሰኘ አዲስ ቴሌቪዥን ጣቢያ መሠረቱ

በዋነኝነት በኢስላማዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ሠሩ የቆዩት “ቢላል ቲቪ”፣ “ጄይሉ ቲቪ” እና “መርከብ ሚዲያ” በመዋሐድ፤ “ነጃሺ ቲቪ” በሚል አዲስ ሥያሜ ቴሌቪዥን ጣቢያ በመመሥረት ወደ ሳተላይት ሊመለሱ መሆኑን በዛሬው እለት የጣቢያው ኃላፊዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቀዋል፡፡

ዛሬ ጁመዐ ታኅሣሥ 25/2017 በአዲስ አበባ ከተማ ስቴይ ኢዚ ሆቴል በተሰጠው መግለጫ፤ መገናኛ ብዙኃኑ ውሕደት መፈጸማቸውን የነጃሺ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አሕመድ ይፋ አድርገዋል፡፡

አቶ ጀማል አሕመድ

ውሕደት የፈጸሙት ሦስት መገናኛ ብዙኃን፤ ለበርካታ ዓመታት “በእስልምና የመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ማኅበረሰቡን በዕውቀት በማነጽና ኢስላማዊ እሴቶችን በማስፋፋት ያለመታከት” የሠሩ መሆኑ በማብሰሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡

በመገናኛ ብዙኃኑ ውሕደት የተመሠረተው ነጃሺ ቲቪ፤ “ከሳምንታት በኋላ አየር ላይ ለመውጣትና በመላው ኢትዮጵያ እና አጎራባች ሀገራት ታዳሚዎች ጋር ለመድረስ ዝግጅቱን አጠናቋል” ተብሏል፡፡ ጣቢያው በሳተላይት ወደ ተመልካቾች የሚደርሰው በኢትዮ ሳት በኩል መሆኑንም ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

ቴሌቪዥን ጣቢያው “በማሳወቅ እና ማስተማር” ዓላማ ብቻ ሳይወሰን፤ “ስምምነትን ማጎልበት፣ የተሳሳቱ መረጃዎችን ማረም እና ማኅብረሰብ ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ ለመፍጠር” የዜና፣ ዳዕዋ እና መዝናኛ ይዘቶችን የሚያካትት እንደሚሆንም የጣቢያው ኃላፊዎች በሰጡት ማብራሪያ ላይ አስረድተዋል፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular