Homeዜናና ወቅታዊዜናሁለተኛው ዓለም አቀፍ የቁርኣን እና አዛን ውድድር በቀጣይ ወር በአዲስ አበባ እንደሚካሔድ...

ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የቁርኣን እና አዛን ውድድር በቀጣይ ወር በአዲስ አበባ እንደሚካሔድ አዘጋጆቹ ገለጹ

በኢትዮጵያ ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የቁርኣን እና አዛን ውድድር በአዲስ አበባ ከተማ በቀጣዩ ጥር ወር እንደሚካሔድ አዘጋጆቹ በዛሬው እለት ገለጹ፡፡ ይህ የተገለጸው ዛሬ ረቡዕ ታኅሣሥ 16/2017 በዘይድ ኢብን ሳቢት የቁርኣን ማኅበር ጽሕፈት ቤት በተሰጠው መግለጫ ነው፡፡

እንደ አዘጋጆቹ ከሆነ፤ የቁርኣን እና አዛን ውድድሩን ጥር 25/2017 በአዲስ አበባ ስታዲየም ለማከናወን ቀን ተቆርጧል፡፡

የዘይድ ኢብኑ ሳቢት የቁርኣን ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ ኡስታዝ ኑረዲን ቃሲም በመግለጫው እንደተናገሩት፤ በቁርኣን ውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ከ60 በላይ ሀገራት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቀዋል፡፡ ውድድሩ ከዚህ ቀደም ከተከናወነው የመጀመሪያ ዙር ውድድር የተሻለ ለማድረግ ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውም ገልጸዋል፡፡

ለዘንድሮው ዓመት ሁለተኛ ዙር የቁርኣን እና አዛን ውድድር ለመታደም ለሚፈልጉ ተመልካቾች ትኬት መዘጋጀቱን ያስታወቁት አዘጋጆቹ፤ ከነገ ሐሙስ ታኅሣሥ 17/2017 ጀምሮ ከተዘጋጁ ቦታዎች ማግኘት እንደሚችሉም ገልጸዋል፡፡

ዘይድ ኢብን ሳቢት የቁርኣን ማኅበር የቁርኣንና የአዛን ውድድሩን ወጪ ለመሸፈን ያስችለኛል ያለውን የገቢ ማሰባሰቢያ በጥቅምት ወር መጀመሪያ አከናውኖ እንደነበር ይታወቃል፡፡

በኢትዮጵያ የመጀመርያው ዓለም አቀፍ የቁርኣን እና የአዛን ውድድር ከሁለት ዓመት በፊት በአዲስ አበባ ስታዲየም መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular