Homeዜናና ወቅታዊዜናየአሜሪካው ዲፕሎማት ሀገራቸው በጋዛ ጉዳይ የያዘችውን አቋም በመቃወም ሥልጣን በገዛ ፍቃድ ለቀቁ

የአሜሪካው ዲፕሎማት ሀገራቸው በጋዛ ጉዳይ የያዘችውን አቋም በመቃወም ሥልጣን በገዛ ፍቃድ ለቀቁ

የአሜሪካው ዲፕሎማት ሀገራቸው በጋዛ ጉዳይ የያዘችውን አቋም በመቃወም ከሥልጣን በገዛ ፍቃድ መልቀቃቸው ታውቋል፡፡ የቀድሞው ዲፕሎማት የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ፍልስጤምን በተመለከተ የሚያቀርቡትን ሪፖርት ችላ ብሏል በማለት ወቀሳ ሰንዝረዋል፡፡  

በፍልስጤም ጉዳይ ሀገራቸው የያዘችውን አቋም በመቃወም ከሥልጣን በገዛ ፍቃድ የለቀቁት፤ ማይክ ኬሲ የተባሉ ዲፕሎማት ናቸው፡፡ ዲፕሎማቱ ለአራት ዓመታት ካገለገሉበት የመንግሥት ሥራ ከወራት በፊት መልቀቃቸውን ለእንግሊዙ ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡

ኬሲ ከጋዜጣው ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ “በየቀኑ በጋዛ ስለሚገደሉ ሕፃናት እየጻፉ ሪፖርት ማቅረብ ብቻ ከበደኝ” ብለዋል፡፡ አክለውም በየቀኑ ሪፖርት ቢቀርብም “ምንም የሚመጣ ለውጥ አለመኖሩ የሕሊና ዕዳ” እንደሆነባቸው በማስረዳት የሥራ መልቀቂያ ያስገቡበትን ምክንት አስረድተዋል፡፡

ዲፕሎማቱ ማይክ ኬሲ የጋዛን ጉዳይ አስመልክቶ በተቀመጡበት የሥራ መደብ መረጃዎችን በማደራጀት ለጆ ባደን አስተዳደር ማቅረብ ይጠበቅባቸው ነበር፡፡ የሚደርሷቸውን መረጃዎች በማደራጀት መፍትሔ እንዲሰጥባቸው “ምክረ ሐሳቦችን ብናቀርብም” ለሁሉም የመፍትሔ ሐሳቦች “የእስራኤል ባለሥልጣናት በዚህ ጉዳይ ሌላ ሐሳብ አላቸው” በሚል ውድቅ እንደሚደረግባቸው ገልጸዋል፡፡

በዚህም የሚሠሩት ሥራ “ፋይዳ ቢስ” ሆኖ እንዲሰማቸው እንዳደረጋቸው ያብራራሉ፡፡ አሜሪካ በፍልስጤም ጉዳይ ምንም ዐይነት ፖሊሲ የላትም የሚል መከራከሪያ ያቀረቡት ዲፕሎማቱ ኬሲ፤ “የምናስፈጽመው የእስራኤልን ፍላጎት ነው” ሲል ተናግረዋል፡፡ በአሜሪካው ዲፕሎማት የቀረበውን ቅሬታ በተመለከተ የሚጽፉ በተለይ የመካከለኛው ምሥራቅ ተንታኖች፤ አሜሪካ በቀጣናው በተለይ ደግሞ በፍልስጤም ጉዳይ ተመሣሣይ አቋም በተደጋጋሚ እንደምታንጸባርቅ ገልጸዋል፡፡

በፍልስጤም እና እስራኤል ጉዳዮች የሚሠሩት የመካከለኛው ምሥራቅ ፕሮግራም ዳይሬክተር የሆኑት ኻሊድ አልጊንዲ፤ “በጋዛ በተደጋጋሚ የተኩስ አቁም እንዲደረግ [ከአሜሪካ ባለሥልጣናት] ጋር ብንነጋገርም ሰሚ አላገኘንም” ሲሉ ሁኔታው አስቸጋሪ መሆኑን ለ ዘጋርዲያን ጠቁመዋል፡፡

አሜሪካ ለእስራኤል የጦር መሣሪያ ድጋፍ በማድረግ በቀዳሚነት የምትቀመጥ ሀገር መሆኗን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የጋዛ ጤና ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያመለክተው እስራኤል ባለፉት አስራ አራት ወራት ብቻ ቢያንስ 45 ሺሕ ፍልስጤማዊያንን ገድላለች፡፡ ከእነዚህ መካከል በርካታውን ቁጥር የሚይዙት ሕፃናት እና እናቶች ናቸው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular