Homeዜናና ወቅታዊዜናበሺሕዎች የሚቆጠሩ ሞሮካዊያን ፍልስጤምን በመደገፍ ሠልፍ ወጡ

በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሞሮካዊያን ፍልስጤምን በመደገፍ ሠልፍ ወጡ

በሰሜን አፍሪካ ውስጥ በምትገኘው ሞሮሞ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሠልፈኞች፤ በጋዛ በፍልስጤማዊያን ላይ ይፈፀማል ያሉትን የዘር ፍጅት በመቃወም በአደባባይ ሠልፍ አካሔደዋል።

ትናንት ጁመዓ ከሰላት መልስ በተካሔደው የድጋፍ ሠልፍ፤ የእስራኤል ወታደሮች በንጹሐን ላይ የሚፈጽሙትን ጥቃት የሚያወግዙ መፈክሮች ተስተጋብተዋል። በእለቱ የተካሔደው የድጋፍ ሠልፍ ለ64ኛ ጊዜ የተከናወነ መሆኑን የሚድል ኢስት ሞኒተር ዘገባ ያመለክታል።

ሠልፈኞቹ በጋዛ የሚፈፀመውን የንጹሐን ጥቃት ከማውገዝ በተጨማሪ የእስራኤል ወታደሮች በወረራ የያዙትን የፍልስጤም መሬት ለቅቀው እንዲወጡ ጠይቀዋል።

በዚህ ሠልፍ ላይ የተስተጋባው ሌላኛው ጉዳይ ሞሮኮ ከእስራኤል ጋር በድጋሚ ያደሰችው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ነው። እ.አ.አ በታኅሣሥ 2022 በአሜሪካ አደራዳሪነት በተደረሰው ስምምነት፤ የሞሮኮ እና እስራኤል ባለሥልጣናት ተቋርጦ የቆየ ግንኙነታቸውን ለመመለስ ተስማምተዋል። የእስራኤል መንግሥት ከሞሮኮ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ካደሰ በኋላ ዳግም በጋዛ ጥቃት መክፈቱ የሞሮኮ ዜጎች በመንግሥታቸው ላይ ተቃውሞ እንዲያሰሙ ማድረጉን ዘገባው አመልክቷል።

የእስራኤል ወታደሮች ባለፉት አስራ አራት ወራት በጋዛ በፈፀሙት ጥቃት ቢያንስ 45 ንጹሐንን መግደላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ከተገደሉት መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ሕፃናት እና እናቶች ናቸው። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular