Homeዜናና ወቅታዊዜናአምስት ፍልስጤማዊያን በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ላይ ክስ መሠረቱ

አምስት ፍልስጤማዊያን በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ላይ ክስ መሠረቱ

ነዋሪነታቸው በጋዛ፣ በዌስት ባንክ እና አሜሪካ የሆነ አምስት ፍልስጤማዊያን፤ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት (ስቴት ዲፓርትመንት) ላይ ክስ መመሥረታቸው ታወቀ፡፡

በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ላይ ክሱ የተመሠረተው በግድያ፣ እንግልት እና ከባድ የመብት ጥሰቶች ላይ ለተሰማሩ የውጭ ኃይሎች ገንዘብ ማስተላለፍን የሚከለክለውን የፌዴራል ሕግ ተግባራዊ ማድረግ ባለመቻሉ ነው፡፡ ፍልስጤማዊያኑ ባቀረቡት የክስ መዝገብ፤ ከባለፈው ዓመት መጀመሪያ አንስቶ በጋዛ የተፈጸመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዘርዝረዋል፡፡

ፍልስጤማዊያኑ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት፤ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የመከላከያ ሚኒስቴር የሰብዓዊ መብቶችን ለሚጥሱ የውጭ የፀጥታ ኃይሎች ወታደራዊ ድጋፍ ከመስጠት የሚገድበው ሊአሂ የተሰኘ ሕግ ነው፡፡

የአሜሪካ መንግሥት ይህን ማድረግ ሳይችል በመቅረቱ ለእስራኤል የጦር መሣሪያ በድጋፍ እየሰጠ በአስራ አራት ወራት ውስጥ እስራኤል ወታደሮች ጥቃት ሰንዝረው የገደሏቸው ንጹሐን ቁጥር 45 ሺሕ መድረሱን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡

በጋዛ በተፈጸመው ጥቃት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች የጦር ወንጀል እና ከዘር ፍጅት ጋር የሚተካከል ወንጀል እንደተፈጸመ ይፋ አድርገዋል፡፡

በአምስት ፍልስጤማዊያን የተከፈተውን የክስ መዝገብ በተመለከተ አልጀዚራ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አስተያየት እንዲሰጠኝ ብጠይቅም ምላሽ ማግኘት አልቻልኩም ብሏል፡፡

በመላው ዓለም ለወራት ያህል ጠበቆች እና የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች በጋዛ እና በዌስት ባንክ ውስጥ በፍልስጤማዊያን ላይ የሚፈጸሙ በርካታ ጥሰቶችን በመጥቀስ የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ለእስራኤል ወታደራዊ ድጋፍ ከመስጠት እንዲቆጠቡ ሲጠይቁ ቆይተዋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular