የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን በኢትዮጵያ ጉብኝት ሊያደርጉ መሆኑን ገልጸዋል። አናዶሉ ኤጀንሲ እንደዘገበው ከሆነ ፕሬዝዳንቱ ኢትዮጵያን የሚጎበኙት ከ15 ቀናት በኋላ በሚጀምረው እ.አ.አ የ2025 የመጀመሪያ ሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ነው። ጉብኝቱ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ሶማሊያንም ያካትታል ተብሏል።
የፕሬዝዳንቱ የጉብኝት ዜና የመጣው በሳምንቱ አጋማሽ ታኅሣሥ 3/2017 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሸይኽ ማሕሙድ በአንካራ ውይይት አድርገው ኢትዮጵያ በሶማሊያ ዘላቂ የባሕር መተላለፊያ እንድታገኝ የሚያስችል የንግድ እና የሁለትዮሽ ስምምነት ካደረጉ በኋላ ነው። ይህን ድርድር የመሩት ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን እንደነበሩ ይታወቃል።
ረቡዕ በተፈረመውና በቱርክ ይታገዛል የተባለው ውይይት ከፌብሩዋሪ 2025 በፊት እንዲጀመር ከውሳኔ ተደርሷል። መደበኛው ስምምነት ደግሞ በአራት ወራት ውስጥ ይቋጫል ተብሏል። በሁለትዮሽ ስምምነቶች አማካኝነት የኮንትራት፣ የኪራይና የመሳሰሉት የንግድ ስምምነቶች ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጾ ነበር። (ሚንበር ቲቪ)












