Homeዜናና ወቅታዊዜናበሶሪያ የበሻር አል አሰድ አገዛዝ ከወደቀ አንድ ሳምንት በኋላ ት/ቤቶች ተከፈቱ

በሶሪያ የበሻር አል አሰድ አገዛዝ ከወደቀ አንድ ሳምንት በኋላ ት/ቤቶች ተከፈቱ

በሶሪያ ባለፈው ሳምንት እሑድ ሀገሪቱን ለ24 ዓመታት የመሩትን የበሻር አል አሰድን አገዛዝ መውደቅ ተከትሎ፣ በዛሬው እለት ትምሕርት ቤቶች ዳግም ክፍት መደረጋቸው ታውቋል። በመዲናዋ ደማስቆ ተማሪዎች ወደ ትምሕርት ገበታ የተመለሱት የበሻር አል አሰድ ተቃዋሚዎች በአሕመድ አል ሸራ ተመርተው ሥልጣን ከተቆጣጠሩ በኋላ ነው።

ተቃዋሚዎች የቀድሞውን ፕሬዝዳንት አገዛዝ መጣላቸውን ካሳወቁ በኋላ ሙሐመድ አል በሽር የባለአደራ ጠቅላይ ሚኒስትር ተደርገው እንደተሾሙ ይታወቃል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደተሾሙ ሳምንታዊውን የጁመዓ ሰላት የመሩትም በዚሁ ሳምንት ነው።

ሬውተርስ የዜና ወኪል ይዞት እንደወጣው ዘገባ ከሆነ፣ ዛሬ እሑድ ደግሞ የደማስቆ ትምሕርት ቤቶች ለተማሪዎች ክፍት ተደርገዋል። በሶሪያ ሁሉም ትምሕርት ቤቶች በሀገሪቱ የሥራ መጀመሪያ ቀን እሑድ ክፍት ተማሪዎቻቸውን ለመቀበል ክፍት መደረጋቸውን የሚያመለክተው ዘገባው፣ በትምሕርት ቤቶቹ በርካታ ተማሪዎች ወደ ክፍል ቢገቡም በአንዳንድ አካባቢዎች የተማሪ ወላጆች ልጆቻቸውን ከመላክ ተቆጥበዋል። ለዚህ የተቀመጠው ምክንያት በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ርግጠኛ ባለመሆናቸው ነው።

የሶሪያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት በሻር አል አሰድ፣ ባለፈው ሳምንት ደማስቆ በተቃዋሚዎች ቁጥጥር ከመዋሏ ሰዓታት አስቀድሞ ወደ ሞስኮ መኮብለላቸው መነገሩ ይታወሳል። ሀገሪቱ ያለፉትን 13 ዓመታት ያሳለፈችው በእርስ በእርስ ጦርነት ነው። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular