Homeዜናና ወቅታዊዜናዘምዘም ባንክ ከሳንቲም ፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽን ጋር በአጋርነት ለመሥራት ስምምነት ተፈራረመ

ዘምዘም ባንክ ከሳንቲም ፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽን ጋር በአጋርነት ለመሥራት ስምምነት ተፈራረመ

ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነጻ ያንክ አገልግሎት የሚሰጠው ዘምዘም ባንክ፤ ከሳንቲም ፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽን ጋር በአጋርነት ለመሥራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ፡፡ የፊርማ ሥነ ሥርዐ መርሐ ግብሩ የተካሔደው ዛሬ ሐሙስ ኅዳር 26/2017 በአዲስ አበባ ከተማ ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ነው፡፡

ከባንኩ ጋር የአጋርነት ስምምነት የፈጸመው ሳንቲም ፔይ የተሰኘው የዲጂታል ፋይናንሻል ሥርዓት፤ ተግባራዊ መሆን ለተጠቃሚዎች እና ለደንበኞች በቀላሉ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መሆኑ በመርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡

ስምምነቱን በተመለከተ የተናገሩት የዘምዘም ባንክ ዲጂታል ኃላፊዎች፤ የባንኩ ስትራቴጂ ዕቅድ የዲጂታል ዓለምን በመቀላቀል ተወዳዳሪ መሆን ነው ብለዋል፡፡ የተፈጠረዉ ጥምረት አብር ለማደግ እና በዲጂታል የዘመናዊ ሥርዓት ተፎካካሪ ሆኖ ለመዝለቅ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር መሆንም ተናግረዋል።


ከዘምዘም ባንክ ጋር ስምምነት የተፈራረመው ሳንቲም ፔይ በመተግበሪያ ኪው አር ኮድ እና የፖስ ማሽን መጠቀም የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡ በመርሐ ግብሩ ላይ የሳንቲም ፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽን መተግበሪያን አስመልክቶ ወይዘሮ ቅድስት አያሌው ስለ መተግበሪያው አሠራር ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡  

ዘምዘም ባንክ በዛሬው እለት በተመሣሣይ “ጋሽ ጎ” የተሰኘውን የገንዘብ መላኪያ መተግበሪያ በዛሬው እለት እንደሚያስመርቅ ለ“ሚንበር ቲቪ” የላከው መረጃ ያመለክታል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular