Homeዜናና ወቅታዊዜናለዘጠኝ ዓመታት የተቋረጠው ከኢራን ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ የሚደረግ የአውሮፕላን በረራ በድጋሚ ተጀመረ

ለዘጠኝ ዓመታት የተቋረጠው ከኢራን ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ የሚደረግ የአውሮፕላን በረራ በድጋሚ ተጀመረ

ሳዑዲ ዐረቢያ እና ኢራን ለዘጠኝ ዓመታት ያቋረጡትን ከአንደኛው ሀገር ወደሌላኛው የሚደረገውን የአውሮፕላን በረራ በድጋሚ አስጀመሩ። ሁለቱ ሀገራት በሳምንት ለሁለት ቀናት ከመሻድ ወደ ደማም በረራ ለማድረግ ተስማምተዋል ተብሏል።

ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ በዛሬው እለት በሁለቱ ሀገራት የሚደረገው የአውሮፕላን በረራ ሲጀመር፣ የኢራን አየር መንገድ አውሮፕላን በሰሜን ምሥራቅ ከምትገኘው መሻድ ከተማ በመነሳት ወደ ሳዑዲ ዐረቢያዋ ደማም ከተማ ተሳፋሪዎችን በመጫን መብረር መቻሉን ኢርና የተሰኘው የኢራን ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

ሁለቱ ሀገራት እ.አ.አ በ2016 ያቋረጡትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በድጋሚ የጀመሩት ከአንድ ዓመት በፊት በቻይና አደራዳሪነት ነበር። ይህንኑ ተከትሎ ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ኢራናዊያን ዜጎች ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ለዑምራ ክንውን ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ ማቅናታቸው የሚታወስ ነው።

ሳዑዲ ዐረቢያ እና ኢራን በቻይና አደራዳሪነት ግንኙነታቸውን ለማደስ በኋላ ኢራናዊያን ከዓመታት በኋላ የሐጅ ሥነ ሥርዐት ማከናወንም ችለዋል። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular