የአሜሪካው የሙስሊሞች መብት ተሟጋቹ ‘ዘ ካውንስል ኦን አሜሪካን ኢስላሚክ ሪሌሽንስ’፤ የእስራኤል ባለሥልጣናት የጣሉትን የአዛን ክልከላ በማውገዝ መግለጫ አውጥቷል፡፡ የመብት ተሟጋቹ መግለጫ የመጣው እስራኤል አዛን እንዳይሰማ ክልከላ መጣሏ ከተነገረ በኋላ ነው፡፡
ቀኝ ዘመሙ የእስራኤል የብሔራዊ ደኅንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤን ግቪር እሑድ በይፋ እንደገለጸው፤ መስጂዶች የሚያሰሙት አዛን የታገደው “አይሑድ ነዋሪዎች እንዳይረበሹ ነው”፡፡ ሚኒስትሩ አዛን እንዲሰማ የሚያደርጉ መስጂዶች ላይ ቅጣት እንዲጣል ውሳኔ ተላልፏል፡፡ ቤን ግቪር ይህን ርምጃ የወሰደው ያለ ምክንያት እና ሕገ ወጥነትን የሚወጣ ድምጽን ለመወጋት መሆኑንም ገልጿል፡፡
ከውሳኔው በኋላ የተናገሩት የ‘ዘ ካውንስል ኦን አሜሪካን ኢስላሚክ ሪሌሽንስ’ ኃላፊ ኒሐል አዋድ፤ ድርጊቱ “በመስጂዶች፣ በአብያተ ክርስቲያናት፣ በባሕል ቦታዎችና በሃይማኖታዊ ጽሑፎች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች በሙሉ የፍልስጤምን ባህል ለማጥፋት ለበርካታ ዐስርት ዓመታት የዘለቀው የእስራኤል ዘመቻ አካል” መሆኑን በመግለጽ አውግዘውታል፡፡
አዋድ አያይዘውም የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፤ “የሃይማኖት ነፃነት ላይ ጭቆና እንዲሰፍን አስቻይ ሁኔታ ፈጥሯል” ያሉትን ለእስራኤል መንግሥት የሚሰጡትን ድጋፍ ነቅፈዋል።
የእስራኤል ቀኝ ዘመም ፖለቲከኞች ከዚህ ቀደም በተመሣሣይ የአዛን ድምጽ እንዳይሰማ ለማድረግ፤ አዋጅ እንዲጸድቅ ሲወተውቱ ቆይተዋል፡፡ በቀኝ ዘመም ፖለቲከኞች የተላለፈው ውሳኔ በሌላኛው የፖለቲካ ፓርቲ ዩናይትድ ዐረብ ሊስት አውግዞታል፡፡ የፓርቲው መሪ መንሱር አባስ ውሳኔውን ያሳለፈው ሚኒስትር አብሮ መኖርን ለማበላሸት በተደጋጋሚ ሰሠራ ቆይቷል ብለዋል፡፡
ባለሥልጣኑ ቀድሞም ቢሆን ሙስሊም ጠል የነበሩ እና ወደ እስራኤል መንግሥት ኃላፊነት እሰከመጡበት 2013 ድረስ ይህን መሰል ፀረ ሙስሊም እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ነበሩ መሆናቸውን ሚድል ኢስት ዐይ ዘግቧል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)












