Homeዜናና ወቅታዊዜናየአሜሪካው የሙስሊሞች መብት ተሟጋች ቡድን ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት “የገቡትን ቃል” እንዲያከብሩ...

የአሜሪካው የሙስሊሞች መብት ተሟጋች ቡድን ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት “የገቡትን ቃል” እንዲያከብሩ ጠየቀ

የመብቶች ተሟጋቹ ዘ ካውንስል ኦፍ አሜሪካን ኢስላሚክ ሪሌሽንስ፤ ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ሙሰሊሞችን በተመለከተ የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ ጠየቀ፡፡ የመብት ተሟጋቹ ትራምፕ የጋዛን ጦርነት ለማስቆም እንዲሠሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ዘ ካውንስል ኦፍ አሜሪካን ኢስላሚክ ሪሌሽንስ ይህን የጠየቀው፤ በአሜሪካ ምርጫ የሪፐብሊካን እጩው ዶናልድ ትራምፕ ማሸነፋቸው ይፋ ከተደረገ በኋላ ባወጣው መግለጫ ነው፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ኒሐድ አዋድ ባወጡት መግለጫ፤ በምርጫው የትኛውም ግለሰብ ቢያሸንፍ ችግር እንደማይሆን በመጠቆም፣ “መሠራት ያለበት ጉዳይ መኖሩን” ግን አጽንኦት ሰጥተው ጽፈዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ “በምርጫው ወደ ሥልጣን የወጡ ባለሥልጣናት ሙስሊም መራጮች ያነሷቸውን ጉዳዮች በቅንነት እንዲያጤኑት እንጠይቃለን፣ ይህ ለተመራጩ ፕሬዝዳንት ትራምፕም ይሠራል” ሲሉም አስፍረዋል፡፡

በምርጫው ሙስሊም ጨምሮ ሌሎችም ለትራምፕ ድምጽ የሰጡ አሜሪካዊያን መራጮች ያረጋገጡት ጉዳይ በሀገር ውስጥ ሆነ በውጭ ጥላቻ እና ጦርነት በድጋሚ ማየት እንደማፈልጉ መሆኑንም አያይዘው ገልጸዋል፡፡ በዋና ዳሬክተሩ ትራምፕ ሊሠሩበት ይገባል ሚል ከተገለጹ ጉዳዮች ውስጥ በዋንኝነት የተጠቀሰው የፍልስጤም ነጻነት ነው፡፡  

ኒሐድ አዋድ

ከአሜሪካ ምርጫ አስቀድሞ በቅስቀሳ ወቅት በተለይ በሙስሊም መራጮች ዘንድ ድምጽ አሰጣጡ ላይ ተጽዕኖ ያሳርፋል ተብሎ በጉዳዩ ላይ በሚጽፉ ሲገመት የነበረው የጋዛ ጉዳይ ነው፡፡ የምርጫው ውጤት ይፋ ሲደረግ በተለይ በርካታ ሙስሊም መራጮችን በሚይዘው ሚቺጋን ግዛት ቀደም ብሎ በወጣ የውጤት መግለጫ ትራምፕ ከፍተኛ ድምጽ ማስመዝገባቸው ታውቋል፡፡ በግዛቷ ዴርቦርን አካባቢ ትራምፕን የመጡ ሰዎች አሐዝ 47 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ካማላ ሐሪስ 27 በመቶ ሲያገኙ፣ በሦስተኛ አማራጭነት ሥማቸው ደጋግሞ የተጠቀሰው የግሪን ፓርቲዋ ጂል ስቴይን 21 መቶ ድምጽ ማግኘት ችለዋል፡፡

የፍልስጤም የዘር ግንድ ያላት የሚል ኢስት ዐይ ዘጋቢ ያስሚን አል ሳባዊ በዴርቦርን የዶናልድ ትራምፕን ማሸነፍ የሰሙ እንደ እርሷ ከፍልስጤም ምድር የበቀሉ ሰዎች፣ ደስታቸውን በአደባባይ ሲገልጹ ነበር ብላለች፡፡ በዘገባው የተጠቀሰው ነቢል ሐማሚህ የተባለ የአካባቢ ነዋሪ አሜሪካ ለውጥ እንደሚያስፈልጋት በመግለጽ፣ ለውጡን ሊያመጡ የሚችሉት ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ናቸው ሲል ተናግሯል፡፡

ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫው ማሸነፋቸው ከተረጋገጠ በኋላ ለደጋፊዎቻቸው ባስተላለፉት መልእክት፣ ጦርነት ለማስቆም እንሠራለን ሲሉ ቢደመጡም የጋዛን ሥም አልጠሩም፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ቃለ መሐላ ፈጽመው የፕሬዝዳንትነት መንበሩን ከጆ ባይደን ይረከባሉ ትሎ የሚጠበቀው ጥር 12/2017 ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular