Homeዜናና ወቅታዊዜናበአሜሪካ የሕዝብ እንደራሴ ምርጫ ኢልሃን ዑመር በድጋሚ አሸነፉ

በአሜሪካ የሕዝብ እንደራሴ ምርጫ ኢልሃን ዑመር በድጋሚ አሸነፉ

በአሜሪካ ምርጫ በሚኒሶታ ግዛት ለሕዝብ እንደራሴነት የተወዳደሩት የሶማሊያ የዘር ግንድ ያላቸው ኢልሃን ዑመር በድጋሚ ማሸነፋቸው ታወቀ፡፡ የዴሞክራቲክ ፓርቲ እጩዋ ኢልሃን በምርጫው የረቱት ለእስራኤል ድጋፍ በመስጠት የሚታወቁትን የሪፐብሊካን ዕጩ ዳሊያ አል አቂዲን ነው፡፡

በሠፊ ልዩነት በተጠናቀቀው ምርጫ ኢልሃን ዑመር የመራጮችን 76.4 በመቶ ድምጽ ሲያገኙ፣ አቂዲ ያስመዘገቡት 23.6 በመቶ መሆኑን የአሶሽየትድ ፕረስ ዘገባ ያመለክታል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ ኢልሃን ለሦስተኛ ጊዜ በሕዝብ እንደራሴነት መቀመጫ ማግኘት ችለዋል፡፡

ሙስሊም አሜሪካዊቷ የሕዝብ እንደራሴ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ለእስራኤል ጋፍ በሚቀሰቅሱ ቡድኖች ሀገራቸው የምትሰጠውን የጦር መሣሪያ ድጋፍ ተቃውመዋል በሚል ዘመቻዎች ሲደረጉባቸው የቆዩ ናቸው፡፡ በጋዛ የሚፈጸመውን ጥቃት በማውገዝ የሚታወቁት ኢልሃን፣ የእስራኤል ወታደሮችን የዌስት ባንክ ወረራም ሲቃወሙ ነበር፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ኢልሃን ዑመር የሪፐብሊካን ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ እጩ በሆኑት ዶናልድ ትራምፕ የ9/11ን ክስተት በማቃለል ክስ ቀርቦባቸው ያውቃል፡፡

ኢልሃን ዑመር የሕዝብ እንደራሴ መቀመጫ ባሸነፉበት አሜሪካ፤ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ሲሆን፣ እስካ ረፋድ ድረስ ባለው ውጤት መሠረት የሪፐብሊካን ፓርቲ እጩው ዶናልድ ትራምፕ የዴሞክራቲክ ፓርተዋ ካማላ ሐሪስን ለማሸነፍ ጥቂት ድምጽ እንደቀራቸው የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular