Homeዜናና ወቅታዊዜናየእስራኤልን “ድምጽ ያስተጋባሉ” የተባሉ የዐረቢኛ ቻናሎች ላይ ዘመቻ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ

የእስራኤልን “ድምጽ ያስተጋባሉ” የተባሉ የዐረቢኛ ቻናሎች ላይ ዘመቻ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ

በእስራኤል ላይ የሚደረጉ የኢንቨስትመንት ስምምነቶች እንዲቋረጡ እንዲሁም ዘመቻ የሚያስተባብረው ቢዲኤስ በሚል ምሕጻር የሚጠራው እንቅስቃሴ፤ የቤንያሚን ኔታንያሁ አስተዳደርን ድምጽ ያስተጋባሉ የተባሉ የዐረቢኛ ቻናሎች ላይ አዲስ ዘመቻ እንዲደረግ ጥሪ አቀረበ፡፡

እንቅስቃሴው ዘመቻው ይደረግባቸዋል ካላቸው ቻናሎች መካከል የሳዑዲ ዐረቢያው አል ዐረቢያ እና የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶቹ ስካይ ኒውስ ዐረቢያ ይገኙበታል፡፡

ቢዲኤስ የተሰኘው እንቅስቃሴ ይህንኑ ዘመቻውን ይፋ ያደረገው በዐረቢኛ ቋንቋ በሚያስተዳድራቸው የማኅበራዊ ትስስር ገጾቹ ነው፡፡ እንቅስቃሴው በዐረቢኛ ቋንቋ የእስራኤልን ድምጽ ያስተጋባሉ ያላቸው ቻናሎች አምስት ሲሆኑ፤ በሦስት ሀገራት ንብረትነት የተመዘገቡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ከሳዑዲ ዐረቢያ አል ዐረቢያ፣ ኤምቢሲ እና አል ሐደስ ሥማቸው ሲጠቀስ፣ ስካይ ኒውስ ዐረቢያ እና ሸሒድ ከተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ተካተዋል፡፡ የሊባኖሱ የዜና ኔትወርክ ኤምቲቪም እንዲሁ በዝርዝሩ ውስጥ አለበት፡፡

እንቅስቃሴው ለዘመቻው ምክንያት ነው በሚል ከጠቀሳቸው መካከል የእስራኤልን ጥቃት አብዝቶ በማስተጋባት የዐረቡን ዓለም በተስፋ መቁረጥ ከተውታል የሚለው ይገኝበታል፡፡ በአስረጂነት የቀረበውም በጋዛ የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ እና ሊባኖስ የሚፈጽትን ጥቃት ከእስራኤል አንጻር ያስተጋቡባቸውን ዘገባዎች ነው፡፡

የዘመቻው አስተባባሪዎች ተመልካቾች እነዚህ ቻናሎች ከመመልከት እንዲሁም ሰብስክራይብ ከማድረግ እንዲታቀቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular