Homeዜናና ወቅታዊዜናመላው የከተማዋ ነዋሪ በእሳት አደጋ ንብረት ከወደመባቸው ወገኖች ጎን እንዲቆም የምክር ቤቱ...

መላው የከተማዋ ነዋሪ በእሳት አደጋ ንብረት ከወደመባቸው ወገኖች ጎን እንዲቆም የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ጥሪ አቀረቡ

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሡልጣን አማን፤ መላው የከተማዋ ነዋሪ በእሳት አደጋ ንብረት ከወደመባቸው ወገኖች ጎን እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ፡፡ በከተማዋ ትናንት ጥቅምት 11/2017 ምሽት በተከሰተው የእሳት አደጋ በርካታ ሱቆች በቃጠሎ መውደማቸው ታውቋል፡፡

የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ጥሪውን ያቀረቡት ዛሬ ረፋድ ላይ ባወጡት የሐዘን መግለጫ ነው፡፡ ጥቅምት 11 ምሽት በአዲስ አበባ መርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ ከፍተኛ የእሳት አደጋ ተከስቶ ከባድ ጉዳት መድረሱን በሚያትተው የፕሬዝዳንቱ መግለጫ፤ እሳቱ ባደረሰው አደጋ ምክንያት ንብረታቸውን ላጡ ማኅበራት፣ግለሰቦች እንዲሁም መላው የአደጋው ሰለባዎች ‘አላህ ቀልባችሁን እንዲያረጋጋላቸውና መልካሙን ምትክ እንዲያደርግላቸው’ ምኞታቸውን ገልጸውበታል፡፡

ሸይኽ ሱልጣን በመግለጫቸው የዚህ ዓይነት አሳዛኝ አደጋ ሲደርስ ከመደናገጥ ይልቅ “ወደ አላህ መመለስና ተረጋግቶ ዱዓ ማድረግ” ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

“ሚንበር ቲቪ” በሥፍራው ተገኝቶ መመልከት እንደቻለው፤ በመርካቶ የተከሰተው የእሳት አደጋ ሸማ ተራ ከጃቡላኒ የንግድ ማዕከል ጀርባ ወይም ሽንኩርት በረንዳ በሚባለው ሥፍራ ላይ የደረሰ ነው። በአደጋው በርካታ የንግድ መድሮች መውደማቸውን መመልከት ችለናል፡፡

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከአደጋው በኋላ እንዳሉት ከሆነ የእሳት አደጋው መነሻ ምክንት ላይ ምርመራ እየተደረገ ይገኛል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular