Homeዜናና ወቅታዊዜናየተማከለ “የሸሪዓ አማካሪ ኮሚቴ” እንዲቋቋም የሚያስችል የአዋጅ ድንጋጌ ወደ ተወካዮች ም/ቤት መላኩን...

የተማከለ “የሸሪዓ አማካሪ ኮሚቴ” እንዲቋቋም የሚያስችል የአዋጅ ድንጋጌ ወደ ተወካዮች ም/ቤት መላኩን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተማከለ “የሸሪዓ አማካሪ ኮሚቴ” እንዲቋቋም የሚያስችል የአዋጅ ድንጋጌ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መላኩን አስታወቀ፡፡ የባንኩ ኃላፊዎች የመጨረሻውን የውሳኔ ሐሳብ ለማቅረብ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

የተማለከ “የሸሪዓ አማካሪ ኮሚቴ” እንዲቋቋም የሚያስችል የአዋጅ ድንጋጌ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንደተላከ የተናገሩት፤ የብሔራዊ ባንክ ምክት ገዥ አቶ ሠለሞን ደስታ ናቸው፡፡ ምክትል ገዥው ይህን የተናገሩት ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነጻ አገልግሎት የሚሠጠው ሂጅራ ባንክ “ሐላል ፔይ” የተሰኘ መተግበሪያ ይፋ ባደረገበት መድረክ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ሐያት ሪጀንሲ ጥቅምት 9/2017 በተካሔደው መርሐ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ሠለሞን፤ የአዋጅ ድንጋጌው “ባልተማከለ የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ ምክንያት የሚታዩ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ” የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ቦርዱ እንዲቋቋም በሚያስችለው የአዋጅ ድንጋጌ ላይ በአሁኑ ሰዓት የመጨረሻ የውሳኔ ሐሳብ ለማካተት እየተሠራ መሆኑንም አክለዋል፡፡ ለዚህ ግብዐት እንዲውል በኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር አስተባሪነት ጥናት ተደርጎ መቅረቡንም ምክትል ገዥው በንግግራቸው አንስተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ብሐየራዊ ባንክ መረጃ መሠረት በሀገሪቱ በአሁኑ ሰዓት ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ አገልግሎት የሚሰጡ ባንኮች ቁጥር ስምንት ደርሷል። በመስኮት ደረጃ አገልግሎት የሚሰጡት ደግሞ ሠላሳ ገደማ ናቸው። በባንኮቹ የተከፈተው ሒሳብ 22.5 ሚሊዮን ሲሆን፣ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ 232.71 ቢሊዮን ብር እንዲሁም በብድር የተሰጠው 104 ቢሊዮን ደርሷል።

በዘርፉ አገልግሎት የሚሰጡ ከወለድ ነጻ አገልግለት የሚሱ ባንኮች የሚሰይሙት የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ በተናጠል የሚንቀሳስ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ ባንኮች ውስጥ የሚሰጡ አገልገሎቶች ከእስልምና መርሆች ጋር ተስማሚ መሆናቸውን የማረጋገጥ ሥልጣን የሚወስድ አካል ነው፡፡ በመላው ዓለም ካሉ ሀገራት መካከል ከወለድ ነጻ አገልግሎት ከሚሰጡት ውስጥ የሸሪዓ አማካሪ ቦርድን በመሠየም እ.አ.አ በ1976 የተመሠረተው የግብጹ ፈይሰል እስላማዊ ባንክ፣ በ1978 የተመሠረተው የጆርዳን እስላማዊ ባንክ እንዲሁም በዚሁ ዓመት የተመሠረተው የሱዳኑ ፈይሰል እስላማዊ ባንክ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular