Homeዜናና ወቅታዊዜናኒካራጓ በጋዛ ጦርነት ምክንያት ከእስራኤል ጋር ያላትን ዲፕሎማሲ ግንኙነት አቋረጠች

ኒካራጓ በጋዛ ጦርነት ምክንያት ከእስራኤል ጋር ያላትን ዲፕሎማሲ ግንኙነት አቋረጠች

በማዕከላዊ አሜሪካ ውስጥ የምትገኘው ኒካራጓ እስራኤል በጋዛ ላ በከፈተችው ጦርነት ምክንያት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን ማቋረጧን አስተወቀች፡፡ ሀገሪቱ ውሳኔውን ያስታወቀችው ምክትል ፕሬዝዳንትዋ በኩል ነው፡፡

የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ሮሳሪዮ ሙሪሎ በሀገራቸው ብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው የኒካራጓ ኮንግረስ እስራኤል በጋዛ የምትፈጽመው ጭፍጨፋ አንድ ዓመት መድፈኑን ተከትሎ ርምጃ እንዲወሰድ የሚጠይቅ ውሳኔ ማጽደቁን ገልጸዋል፡፡

የኒካራጓ መንግሥት እስራኤል ከጋዛ በተጨማሪ በሊባኖስ ላይ መሰንዘር የጀመረችውን ጥቃት በማውግዝ፤ ይህ እንቅስቃሴ ለሶሪያ፣ የመን እና ኢራን ጭምር አስጊ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

እንደ ኒካራጓ ሁሉ፤ በተለያዩ የአሜሪካ አካባቢዎች እስራኤልን የሚቃወሙ ሀገራት ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ሔዷል፡፡ የላቲን አሜሪካ ሀገራቱ ብራዚል፣ ኮሎምቢያ እና ቺሊ በዚህ ዝርዝር ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ከሀገራቱ መካከል ኮሎምቢያ ከእስራኤል ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያቋረጠችው ቀደም ብላ ነው፡፡ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጎስታቮ ፔትሮ የህን ውሳኔ ያሳፉት ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ነበር፡፡ ፕሬዝዳንት ፔትሮ የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንሁን በዘር ጭፍጨፋ ከሰዋል፡፡ የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ሉላ ደ ሲልቫም ከጋዛ ጋር በተገናኘ በእስራኤል የሚገኙትን የሀገራቸውን አምባሳደር የጠሩት በተመሣሣይ ወር ነበር፡፡

ኒካራጓ ከእስራኤል ጋር ያላትን ዲፕሎማሲ ግንኙነት ማቋረጧን ባስታወቀችበት በዚህ ወቅት፤ እስራኤል እ.አ.አ ከጥቅምት 7/2023 ወዲህ የገደለቻቸው ንጹሐን ፍልስጤማዊያን ቁጥር 42 ሺህ 289 ደርሷል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular