Homeየቲቪ ፕሮግራሞችደቡብ አፍሪካ እስራኤል በጋዛ “የዘር ማጥፋት ድርጊቶች እየፈጸመች ነው” ስትል በዓለም አቀፉ...

ደቡብ አፍሪካ እስራኤል በጋዛ “የዘር ማጥፋት ድርጊቶች እየፈጸመች ነው” ስትል በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ያቀረበችውን ክስ ቦሊቪያ ተቀላቀለች

የደቡብ አሜሪካዋ ሀገር ቦሊቪያ፤ ደቡብ አፍሪካ እስራኤል በጋዛ “የዘር ማጥፋት ድርጊቶች እየፈጸመች ነው” ስትል በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ያቀረበችውን ክስ መቀላቀሏ ይፋ ተደረገ፡፡ ይህንኑ የሀገሪቱን ውሳኔ መቀመጫውን ስዊዘርላንድ ሔግ ከተማ ያደረገው ፍርድ ቤት አስታውቋል፡፡

 ፍርድ ቤቱ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፤ ቦሊቪያ ክሱን ያቀረበችው ማክሰኞ እለት ነው፡፡ በሀገሪቱ የቀረበው የክስ ማመልከቻ እስራኤል በጋዛ ላይ ባካሄደችው ጦርነት ዓለም አቀፍ የዘር ማጥፋት ስምምነትን በመጣስ “የዘር ማጥፋት ድርጊት” ፈጽማለች የሚል መሆኑ ተገልጿል፡፡ ውሳኔው ቦሊቪያን ተመሣሣይ ክስ ካቀረቡት ከኮሎምቢያ፣ ከሊቢያ፣ ከስፔን፣ ከሜክሲኮ፣ ከኒካራጓ እና ከቱርክ ጎራ አሰልፏታል፡፡

ደቡብ አፍሪካ በፍርድ ቤቱ የከፈተችው መዝገብ፤ እስራኤል በዘር ማጥፋት ድንጋጌ ስር የተቀመጡትን ደንቦች ጥሳለች በሚል የቀረበ ነው፡፡ በ84 ገጽ ተዘርዝሮ የቀረበው ክስ “በእስራኤል የተፈጸሙ ወንጀሎች በድርጊታቸው የዘር ማጥፋት ጠባይ” ያላቸው መሆኑን ይገልጻል፡፡ ምክንያቱም ሲያስረዳም ፍልስጤምን እና ፍልስጤማውያንን ሁሉ ሆን ብሎ “ለማጥፋት እና ለማውደም የታቀደ ተግባር ስለሆነ” ነው የሚል ሠፍሮበታል፡፡

ክሱ የቀረበለት የተባበሩት መንግሥታት የሕግ አስፈጻሚ አካል የሆነው ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት፤ መቀመጫውን ኔዘርላንድስ ሔግ ከተማ ያደረገ ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ ሀገራት መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ ሲቀርብለት ምርመራ አድርጎ ብይን የሚሰጥ ነው፡፡ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ሕግ ነክ ጉዳዮች ላይ እንዲሁ ምክር ይለግሣል። ሆኖም ለትግበራው ማስገደድ የሚችልበት ሕጋዊ መሠረትም ሆነ አቅም የለውም በሚል የሚተች ነው፡፡

በዚህም ፍርድ ቤቱ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር መገባደጃ ላይ እስራኤል በደቡባዊው የጋዛ ከተማ ራፋ የሰነዘረችው ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም በእስራኤል ባለሥልጣናት ችላ ተብሏል፡፡ ይህ የእስራኤል ድርጊት እንደ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባሉ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ተቃውሞ ቀርቦበታል፡፡

በትናንትናው እለት ለዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ክስ ያቀረበችው ቦሊቪያ፤ ከአንድ ዓመት ገደማ በፊት ከእስራኤል ጋር ያላትን የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋርጣለች፡፡ የቦሊቪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በወቅቱ ለውሳኔው መነሻ የሆነው እስራኤል በጋዛ በምትፈጽመው “ጠበኛ እና ያልተመጣጠነ” የኃይል አካሔድ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የእስራኤል ባለሥልጣናት የቦለቪያን ውሳኔ ከአሸባሪነት እንዲሁም ለኢራን እጅ ከመስጠት ጋር አገናኝተውት ነበር፡፡

እስራኤል ባለፈው አንድ ዓመት ጊዜ ውስት በጋዛ በፈጸመችው ጥቃት ከ42 ሺሕ በላይ ንጹሐንን ገድላለች፡፡ ከእነዚህ መካከል በርካታ ቁጥር የሚይዙት ሕጻናት እና እናቶች ናቸው፡፡  (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular