ያለፉትን ስምንት ወራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት የሠሩት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ፤ በዛሬው እለት የኢፌዴሪ አዲሱ ፕሬዝዳንት ተደርገው ተሰይመዋል፡፡ አምባሳደር ታዬ በፕሬዝዳንትነት የተሰየሙት የቀድሞዋ ፕሬዝዳንት ሣሕለወርቅ ዘውዴ የሥልጣን ጊዜ በመጠናቀቁ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የአምባሳደር ታዬ ፕሬዝዳንትነት ይፋ የተደረገው የሕዝብ ተወካዮች እና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ዛሬ ሰኞ መስከረም27/2017 እያካሄዱት በሚገኘው የጋራ ስብሰባ ላይ ነው፡፡
ይህንኑ ተከትሎ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከቀድሞዋ ፕሬዝዳንት ሣሕለወርቅ ዘውዴ የሥልጣን ርክክብ አድርገዋል፡፡ አዲሱ ፕሬዝዳንት በምክር ቤቱ በአምስት ድምጽ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው የሰየሙት፡፡
ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የተወለዱት በጎንደር ደባርቅ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በእንግሊዝ ሌስተር ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካ ሣይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ያጠኑት ፕሬዝዳንት ታዬ፤ ለበርካታ ዓመታት ሀገራቸውን በዲፕሎማትነት አገልግለዋል፡፡ ከዛሬው ሹመት አስቀድሞ ለወራት ወደሠሩበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሳይመጡ፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልእክተኛ በመሆን የሠሩ ናቸው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)












