Homeዜናና ወቅታዊዜናበኮርኔል ፍልስጤምን በሚደግፍ ሠልፍ ላይ ተሳትፏል በሚል እገዳ የተጣለበት የዶክትሬት ተማሪ ውሳኔ...

በኮርኔል ፍልስጤምን በሚደግፍ ሠልፍ ላይ ተሳትፏል በሚል እገዳ የተጣለበት የዶክትሬት ተማሪ ውሳኔ እንዲሻር ተጠየቀ

በአሜሪካው ኮርኔል ዩኒቨርሲቲ፤ ፍልስጤምን በሚደግፍ ሠልፍ ላይ ተሳትፏል በሚል እገዳ የተጣለበት የዶክትሬት ተማሪ ውሳኔ እንዲሻር ሺሕዎች በፊርማ ጠየቁ፡፡ በፊርማ ማሰባሰቡ ላይ ከዐሥር ሺሕ በላይ ሰዎች ተሳትፈዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ፍልስጤምን በሚደግፍ ሠልፍ ላይ ተሳትፏል በሚል እገዳ የተጣለበት የዶክትሬት ተማሪ ውሳኔ እንዲሻር ከዐሥር ሺሕ ሰዎች የጠየቁት ባለፉት ቀናት ነው፡፡ የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪ የነበረው የዘር ግንዱ ከጋምቢያ የሚመዘዘው የእንግሊዝ ዜግነት ያለው ሞሞዱ ታል የሚባል የሠላሳ ዓመት ግለሰብ ነው፡፡

እግዱ እንዲነሳ የሚጠይቀው ፊርማ ማሰባሰብ፤ የትምሕርት ክፍሉን አባላት እና ሠራተኞችን ባቀፈው በኮርኔል ኮሌክቲቭ ፎር ጀስቲስ ኢን ፓለስታይን አስተባባሪነት እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

አስተባባሪዎቹ ዩኒቨርሲቲው አሠራሩን ባልተገባ መንገድ ጥቅም ላይ አውሎታል በሚል አካሔዱን ተችተዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በአፍሪካን ስተዲስ ትምሕርት ክፍል ጥናቱን የሚሠራው ሞሞዱ ታል፤ ፍልስጤምን የሚደግፈው ሠልፍ ላይ የተሳተፈው ባለፈው ዓመት ነበር፡፡

ሠልፉን በተመለከተ ዩኒቨርሰቲው ባወጣው መግለጫ ላይ፤ ተማሪዎች ፖሊስን ሲገፈትሩ ነበር በሚል ክስ አቅርቧል፡፡ በወቅቱ በዩኒቨርሰቲው በተከናወነ ኤግዚሽን ላይ የተገኙ እንግዶችም እንዲሸበሩ ተደርገዋል በሚል ዩኒቨርሰቲው ተማሪዎቹን ወቅሷል፡፡

ሆኖም እግድ የተላለፈበት ሞሞዱ ታል የቀረበውን ክስ አስተባብሏል፡፡ የኮርኔል ዩኒቨርሲቲ ኃላፊዎች ከእንግሊዝ ወደ አሜሪካ ያመራውን የዶክትሬት ተማሪ ወደመጣበት እንዲመለስ የማድረግ ሕጋዊ ሥልጣን ባይኖረንም ከተማሪነት መዝገብ ላይ መሠረዝ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

ሚድል ኢስት ዐይ ይዞት እንደወጣው ዘገባ ከሆነ፤ ዩኒቨርሲቲው ሞሞድን ወደ ሀገሩ መመለስ ባይችልም፤ ሥሙን ከተማሪነት መዝገብ ከሠረዘው አሜሪካ ውስጥ መቆየት አይችልም፡፡ ለዚህም ተማሪው በአሁኑ ወቅት ውሳኔውን በመቃወም ይግባኝ ጠይቆ እየተጠባበቀ ይገኛል፡፡ ሞሞድ ታል በሀገሪቱ ውስጥ መቆየት የማይችለው የተሰጠው ቪዛ የትምሕርት በመሆኑ ነው ተብሏል፡፡

ይህንኑ ተከትሎ የጥቁር መብት ተሟጋች ቡድኖችም ከጋምቢያዊው ጎን በመቆም ድምጻቸውን እያሠሙ መሆኑ ታውቋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular