Homeዜናና ወቅታዊዜናበጅቡቲ የባሕር ዳርቻ ፍልሰተኞችን የጫኑ ጀልባዎች ሰጥመው ቢያንስ 45 ሰዎች ሞቱ

በጅቡቲ የባሕር ዳርቻ ፍልሰተኞችን የጫኑ ጀልባዎች ሰጥመው ቢያንስ 45 ሰዎች ሞቱ

በጅቡቲ የባሕር ዳርቻ አፍሪካዊያን ፍልሰተኞችን የጫኑ ጀልባዎች ሰጥመው ቢያንስ 45 ሰዎች መሞታቸውን የተባበሩት መንግሥታት የፍልሰተኞች ኤጀንሲ (አይኦኤም) አስታውቋል፡፡

ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት እንዳስታወቀው ከሆነ፤ ከየመን የተነሱት ጀልባዎቹ 310 ሰዎችን አሳፍረው ነበር፡፡ ድርጅቱ በኤክስ ገጹ ባሠፈረው ማስታወሻ፤ ለድንገተኛ ጊዜ ሠራተኞች ድጋፍ እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡ በዚሁ ማስታወሻ ላይ በፍለጋ እና የነፍስ አድን ሥራው እስካሁን ድረስ 32 ከአደጋ የተረፉ ፍልሰተኞች ተገኝተዋል ብሏል፡፡

የጅቡቲ የባሕር ዳርቻ ጠባቂዎች እንዳሉት ከሆነ ደግሞ ከሰኞ አንስቶ ባደረጉት የማፈላለግ ሥራ 115 ሰዎች በሕይወት ተርፈው የተገኙ ቢሆንም፤ አሁንም ድረስ በርካታ ፍልሰተኞች ደብዛቸው ጠፍቷል፡፡

ጀልባዎቹ በጅቡቲ ሰሜናዊ ምዕራብ ኮር አንጋር ክልል አቅራቢያ ከሚገኘው የባሕር ዳርቻ 150 ሜትር ወይም 492 ጫማ እንደሰጠሙ የባሕር ዳርቻ ጠባቂዎቹ መግለጻቸውን የአይኦኤም መረጃ ያመለክታል፡፡ የአስከሬን ከረጢቶችን የያዙ የባሕር ዳርቻ ጠባቂዎች “የነፍስ አድን ሥራውን እስከመጨረሻው ድረስ እንደምንቀጥል እናረጋግጣለን” ሲሉ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ላይ በተመሳሳይ ሕፃናትን ጨምሮ ቢያንስ 38 ሰዎችን የጫነ ጀልባ  ቀይ ባሕርን ተሻግሮ ሲጓዝ በጅቡቲ የባሕር ዳርቻ ላይ በመስጠሙ የተሳፋሪዎች ሕይወት አልፏል። በሰኔ ወር እንዲሁ በዚሁ መንገድ ቢያንስ 49 ሰዎች ሞተዋል፡፡ በዚህ ጉዞ ከተሳፈሩት መካከል አብዛኛዎቹ ከኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የሔዱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ነገር ግን ይህ የፍልሰተኞች ማቋረጫ በረድኤት ድርጅቶች እጅግ በጣም አደገኛ እና የተጨናነቀ ተብሎ የሚገለጽ ነው፡፡ “የምሥራቅ መንገድ” በሚል ሥያሜ የሚጠራው ይህ ማቋረጫ፤ የሕገ ወጥ ሰዎች አዘዋዋሪዎች በሥፋት የሚርመሰመሱበት አካባቢ መሆኑም ይነገራል፡፡  

አይኦኤም በ2023 ወደ 400 ሺሕ ገደማ በምሥራቅ መንገድ ሲሻገሩ መመዝገቡን አስታውቋል፡፡ በዚያው ዓመት ወደ 700 ገደማ ሰዎች ደግሞ መሞታቸው ተረጋግጧል አልያም በሕይወት ይኑሩ ወይም ይሙቱ ማወቅ አልተቻለም፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular