Homeዜናና ወቅታዊዜናበ2016 የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላመዘገቡ ተማሪዎች ነጻ የት/ት ዕድል...

በ2016 የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላመዘገቡ ተማሪዎች ነጻ የት/ት ዕድል ሊሰጥ ነው

በ2016 የትምሕርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ላመዘገቡ ተማሪዎች ነጻ የት/ት ዕድል ሊሰጥ መሆኑን ያስታወቀው አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው። ዩኒቨርሲቲው ነጻ የትምህርት ዕድል የሚሰጠው 500 እና ከዚያ በላይ ላስመዘገቡ 200 ተማሪዎች መሆኑን ገልጿል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይህን ያስታወቀው ዛሬ ረቡዕ መስከረም 8/2017 ነው። ዩኒቨርሲቲው ነጻ የትምህርት ዕድል የሚሰጣቸው 200 ተማሪዎች የሚለዩት በውድድር መሆኑን በመግለጽ፣ የትምህርት እድሉ ዶርሚታሪና የካፌ አገልግሎትን ያካትታል ብሏል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ የመጀመርያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ እንዲሆን ውሳኔ ከተላለፈ በኋላ ተማሪዎችን በራሱ የቅበላ ሥርዓት ተቀብሎ እንደሚያስተምር መግለጹ የሚታወቅ ነው። ዩኒቨርሲቲው ዛሬ እንዳሳወቀው፣ በቅርቡ ያዘጋጀውን የተማሪዎች መግቢያ ፈተና እንደሚሰጥም ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም በነበረው አሠራር በየዓመቱ ሰባት ሺሕ ገደማ አዳዲስ ተማሪዎችን እንደሚቀበል መረጃዎች ያመለክታሉ። በቀድሞው አሠራር መደበኛ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው የሚገቡት፣ ልክ እንደሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉ የትምህርት ሚኒስቴር በሚያደርገው ምደባ ነበር። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ በሚተገብረው ራስ ገዝነት አስቀረዋለሁ ያለው ይህ አሠራር ነው።

ዩኒቨርስቲው በተያዘው የትምህርት ዘመን የቅደመ ምረቃ ተማሪዎችን አወዳድሮ የሚያስገባው መንግሥት በሚመድብለት በጀት ሲሆን፣ ከዚህ ውጪ ደግሞ ክፍያ እየፈጸሙ በዩኒቨርሲቲው የሚማሩ ተማሪዎች ይኖራሉ ተብሏል።

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular